Monthly Archives: October 2014

ሰማያዊ ህዝቡ በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንዲሆን ጥሪ አቀረበ (ይኼኔ ነው እንግዲህ …)

ሰማያዊ ፓርቲ ጥቅምት 18/2007 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ አፋኙን ስርዓት በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንዲሆን ጥሪ አቀረበ፡፡ ‹‹የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል›› ያለው የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ ገዥው ፓርቲ ከዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መልኩ አፋኝ መዋቅሩን በማናለብኝነት እያስፋፋ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለማናቸውም አስተዳደራዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሀይልን በመጠቀም ለመደፍጠጥና ለማጥፋት ቆርጦ በመነሳት ፍፁም አምባገነንነቱን ገፍቶበት የበርካቶች ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ ገልጾአል፡፡ መግለጫው ለስርዓቱ አፋኝነት በምሳሌነት ካነሳቸው መካከል በአለፈው ክረምት ወራት ጀምሮ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰጠው የግዳጅ ስልጠና የሚገኝበት ሲሆን በስልጠናው ስነ ምግባር በጎደለው መልኩ የጥላቻ ዘመቻ በማካሄድ የሃሳብ ልዩነትን የማስተናገድ ፍላጎቱ ሙሉ ለሙሉ እንደተዳፈነ ያሳየ ነው ብሎታል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን ስልጠናዎች እጅግ በቅርበት ሲከታተላቸው የቆየ መሆኑንና ከጅማሬውም ተቃውሞውን በይፋ መግለጹንም መግለጫው አውስቷል፡፡ ፓርቲው በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው የማሳደድ እርምጃ፣ በነጻው ፕሬስ ላይ የተፈጸመው አፈና የስርዓቱን መበስበስ እና አፋኝ አምባገነንነትን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መቀጠል መምረጡን ግልጽ አመላካች ነው ብሏል፡፡ ‹‹እጅግ የከፋውና እየተባባሰ የመጣው ከፍተኛ አደጋ ያዘለ ችግር ያለው አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄ እያነሱ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በሀይል ለመግዛት ቆርጦ መነሳቱ ነው›› ያለው መግለጫው በተለይ በኦጋዴን በርካታ ዜጎች በመንግስት ሀይሎች ህይወታቸው መቀጠፉ ሳያንስ ሬሳቸው እንኳን ክብር በሌለው ሁኔታ መሬት ለመሬት እየተጓተተ ባደባባይ ሰብአዊ መብት ሙሉ ለሙሉ መጣሱን አውስቷል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላም የህወሓት ሰዎች መሬት በሕገ-ወጥ መንገድ መቀራመታቸውን የተቃወሙ በርካታ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ሁነት ሀገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ እያመራች ለመሆኑ አመላካች ነው ሲል ገልጾአል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ገዥው ፓርቲ በህዝብ ላይ የሚፈጽመውን በደል በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ያስታወቀው መግለጫው ‹‹የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት መላው የሀገሪቱ ህዝብ፣ በውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ለሀገር ተቆርቋሪ ተቋማት እንዲሁም በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ስር ሆናችሁ ለውጥን የምትሹ ወገኖች ሀገራችንን ወደ አደጋ እየወሰዳት ያለውን አፋኝ ስርዓት በቻላችሁት ሁሉ በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንድትሆኑ›› ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንጭ:

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35796

ከእስክንድር ነጋ ፍሬዎች አንዷ (ለትውስታ)

Libya’s Gadhafi and Ethiopia’s EPRDF

Eskinder Nega የካቲት 2011 እ.ኤ.አ የወጣ

አሜጋ ነኝ እንደወረደ አቅርቤዋለሁ

Strange as this may sound, there is a mainstream in the unsanctioned confederacy of dictators. Whether of the present times or from the distant past, the mainstream dictator is usually decidedly understated, more often than not a loner, eccentric in private habits, and almost as a trademark, lives in a complex world of paranoia.

Moammar Gadhafi indeed shares some of these traits, but also markedly stands out as part of a glitzy species much disdained by the cool mainstream: the buffoon dictators.

Hitler and Mussolini popularized the buffoon species. They also represent its two sub-specious: the harmful and harmless genres.

History will remember Mussolini more for his absurd theatrics and blunders than the harm he caused. Hitler’s outlandish public tantrums and speeches, on the other hand, are a footnote to the epic tale of moral and physical damage he wrought on humanity.

Until Tuesday, Gadhafi belonged more with Mussolini than Hitler. Aside from the Berlin and Lockerbie bombings in a 40 years reign, the world tolerated Gadhafi with bemused indifference. The international media, for their part, seemed permanently enthralled by his blonde Ukrainian female nurse and gun-totting female bodyguards.

Come February 22, 2011, a day after Libya was overwhelmed by people power, however, the world was suddenly confronted with a new, murderous Gadhafi that was much more than a buffoon. Speaking from the doorsteps of his Tripoli residence once bombed by US air-strikes in the 1980s, he was at times shouting, pounding his fists on a podium, and intermittently losing his stream of thought as he scolded his nation’s democratic aspiration.

But his instruction to supporters, militiamen and thousands of mercenaries in his pay came out clearly. There was no haziness here. “You men and women who love Gadhafi….get out of your homes and fill the streets. Leave your homes and attack them (the protesters) in their lairs,” he thundered.

In a nation where tribal loyalties figure prominently in politics, it was also a subtle call to his kins to defend him. But those who
responded, according to eyewitnesses on Al-Jezzera, were disproportionately his mercenaries.(Sorry EPRDF!)

Divide and rule has lost its magic. A new era has dawned in Libya.

The Libyan protests began on the evening of February 15 by about 2000 people. The number of protesters roughly doubled as passersby and activists joined them. The regime reacted with a firm determination to discourage further defiance of its demonstration ban. Up to ten percent of the demonstrators were seriously brutalized. Many more suffered lesser injuries.

As has recently happened elsewhere in the Middle East, state violence unexpectedly and unusually bred fierce public defiance. There were more outraged protesters in Benghazi, Libya’s second city, the next day. And the protests spread to other cities.

As is the case in all authoritarian countries, including Ethiopia, Gadhafi’s security networks, though one of the most far-reaching in Africa, were simply not large enough—nor could they ever be—to contain simultaneous uprisings in dozens of cities across the country. They lost half the country in 48 hours.

Poor Gadhafi was stunned beyond belief.

This is the scenario that will most probably confront the EPRDF if protests are to break out in Ethiopia. A parallel event, albeit on a smaller scale, had already happened in November 2005 when half a dozen cities exploded at almost the same time. The EPRDF was almost, but not quite, stretched to the limit.

Add a few more cities this time around, and crucially, unlike 2005, with a public that will no doubt be adamantly determined to prevail, EPRDF will be hard pressed to control Addis Ababa, Dire-Dawa and Baher Dar, the nation’s three largest urban areas, at the same time.

With east Libya serving as the inspiring model, the specter of whole regions liberating themselves within 48 to 72 hours of protests breaking out is now entirely plausible. Ethiopians in Addis and across the regions are mesmerized by events in the Arab world as never before, and each dramatic twist of events seems to mischievously broaden the possibilities at home. More trouble than it could possibly handle is brewing for the EPRDF.

The reaction of Libya’s professional military to the rise of people power has by now become conventional in North Africa. Faced with a choice between mass murder and continued loyalty to the regime, it opted, as had its Tunisian and Egyptian counterparts, to switch sides.

Unfortunately, the balance of power does not lie exclusively with the professional military in Libya. Much to the delight of Gadhafi, his disdain of a powerful professional military has finally been vindicated. Wary of a potential coup, he had for long pampered and better armed his paramilitaries and mercenaries. He will only be convincingly beaten when they finally abandon him.( They most probably will.)

The military is all the EPRDF has in Ethiopia. There are no powerful paramilitaries or mercenaries to counterweigh the might of the army. Only its forceful intervention on either side in the event of protests, or its neutrality, as was the case in Egypt until the very last moments, will sway the balance of power. In the unlikely event that it will remain fiercely loyal to the EPRDF in the face of nation-wide mass protests, civilian fatalities that run in the low hundreds, as is offically the case for the 2005 post-election riots, will be too much for the international community. This is not 2005.

But whatever the casualty figures, perhaps no country will suggest the kind of military intervention which the British have proposed in Libya in recent days. Nonetheless, a belligerent EPRDF is doomed to a Pyrrhic victory, if that is indeed the final outcome, which will irremediably rupture its indispensable relationship with the West. And this will inevitably mark the beginning of the end for the historical enigma that is the EPRDF. There is no way for it to come out the winner from a violent clampdown.

Gadhafi used every means at his disposal to suppress the protests. Appallingly, artillery, helicopter gunship, and incredibly, even anti aircraft missiles were fired directly at protesters. But to no avail. In Bengahzi, hundreds of thousands of defiant protesters turned on the regime. In smaller towns, the frenzy of the people was harsher.

As casualty figure reportedly climbed to around a thousand, the surge of defections by once Gadhafi loyalists, which started in the military, encroached with no less ferocity to the civilian sector. Fuming Ministers, Ambassadors and religious leaders were soon urging rebellion against the regime.

EPRDF could count on even less officials to stay faithful to it. This will be particularly true of its diplomats. “Ethiopian embassies representing the people” will most probably pop up around the globe. Perhaps the only faithful embassy left will be the one in Beijing. But nothing is certain even there. After all, it is Gadhafi’s most dependable comrade-in-arms of four decades who defected first in Benghazi.

All in all, the message to the EPRDF from Libya is crystal clear: don’t fight change. You will not win.

WE NEED YOUR HELP!

God willing, come Tuesday, my first article in Amahric will appear on this website. The Amharic articles are primarily intended for readers in Ethiopia.

The Ethiopian public is more than ever desperate to hear from the people it knows and trusts. I need your help to connect with thousands who know and trust me.

Facebook is the ideal way to reach readers in Ethiopia at the moment. All Ethiopian websites, including, of course, this one, are blocked in Ethiopia.

I urge you to post my Amharic articles on your Facebook pages. Post it on newsfeeds, send it by message to friends in Ethiopia, do everything to get the message in to Ethiopia. Do the same for other articles you like.

Fight tyranny from your PC!

የቀደሞው የኦነግ አመራር ዶ/ር ዲማ ነጋዎ በ24 ሰዓት ውስጥ ከኢትዮጵያ እንዲለቁ ተባለ

Mereja.com በትላንትናው ዕለት እንደዘገበው ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ዶ/ር ዲማ ነጋዎ ከሃገር እንዲለቁ ትእዛዝ ደረሳቸው። ባሁን ሰዓት ምንጩ እንደሚያመለክተው ከሃገር ወጥተዋል።

ዝርዝሩን እንደሚከተለው ከድረ-ገፁ  አውርጀዋለሁ

አሜጋ ነኝ

Dr. Dima Nogo, the second in command of Oromo Democratic Organization (ODF), has been ordered by TPLF security to leave the country within 24 hours.

An anonymous source has informed us that Dr. Dima was said to have arrived in Ethiopia for the funeral of late Aadde Tsehay Tolasa, the wife of late Gudina Tumsa, religious leader and Oromo nationalist. Sources claim Dr. Dima intended to discuss with the Ethiopian regime about the terms of ODF’s plan to enter Ethiopian domestic politics.

Dr. Dima was seen with Obbo Abba Dulaa Gammada at the funeral ceremony. He also informally met Obbo Muktar Kedir, the president of Oromia regional state on the same ceremony. However, both OPDO and TPLF senior leaders declined Dima’s request for official meeting.They instead sent a mid-level official, Faysal Aliy who was formerly working at Washington DC embassy but currently head of the diaspora affairs department within ministry of foreign affairs. This made it clear that EPRDF/OPDO does not want to deal with ODF within domestic political framework yet. Later on, it is believed discussions broke down. Although the details of the terms, both by ODF, and EPRDF, are not entirely known to the public, sources close to the matter indicate there is strong disagreement.

EPRDF/OPDO wants to see ODF to completely distance itself from any OLF legacy including the famous OLF [Oromo] flag. It wants to see ODF denounce past ‘’atrocities’’ and current OLF ideologies and armed struggle. Above all, EPRDF/OPDO demands all ODF members give up their foreign citizenship for Ethiopian passport. Although Dr Dima signaled willingness to accept these terms, he was not able to get green light from the remaining ODF leaders to enter into official agreement with TPLF.

ODF’s demands include amnesty given to leadership for their role within OLF. They also asked for the their party to be legalized and allowed participation in the next election.EPRDF/ODPO dropped the demands. After Dima informed Faysal his inability to secure consent from ODF leaders to accept the government’s precondition, intelligence officers ordered him to leave the country in 24 hours. He has now left . What will becoming of the ODF plan to return us hangs in limbo.

Source: Anonymous

http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=88783&sid=f1c7421230892bb981ae2ae8193984a7

በአርባ ጉጉ እና አካባቢው በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም – ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን

(24/10/2014) ሞረሽ ወገኔ

moresh

የባህል ማህበር በስዊድን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ከሸገር ራዴዮ ጣቢያ ጋር በ09/08/2014 ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ምንም እንኳ አማራውን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ እርስ በራሱ የተምታታ ቢሆንም፣ አማራውን ህዝብ የለም ከማለት አልፈው በአርባ ጉጉ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክደዋል። የፕሮፌሰር መስፍን ክህደት ’እስላም ኦሮሞዎች ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ነበር የገደሉት’ ለማለት ከሆነ፣ ሀቁና መረጃዎቹ ከፕሮፌሰር መስፍን ክህደት ጋር እንደማይጠጣሙ በተከታታይ መረጃዎችን እየመዘዝን የአርባ ጉጉን እልቂት ለማቅረብ እንሞክራለን። ወይም ጉልበታቸው ለፈረጠመ ወንጀለኞች መውጫ ቀዳዳ በመፈብረክ የተለመደው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ”የወንድ በር እንስጥ” ፍልስፍናም ከሆነ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ያልተፈጸመና ያልተደረገ አያደርገውም ልንላቸው እንገደዳለን። ከአባሎቻችንና ከደጋፊዎቻችን ጋር ለመወያየት የግብዣ ወረቀት ከላክን በሗላ፣ ከስብሰባው በፊት በአማራው ህዝብ ላይ በአርባ ጉጉ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፕሮፌሰሩ መካዳቸው ብዙዎችን እንዳስቆጣቸው መልክት ሲደርሰን፣ እኛም አንድን ሰው ከሀዲ ከማለታችን በፊት መረጃዎችን አቅርቦ ፍርዱን ለአንባቢ ለመተው፣ በጊዜው የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት ለኢህአዴግ፣ ለውጭ መንግስታት ዲፕሎማቶችና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስ ያወጣውን የአቋም መግለጫ ከሞላ ጎደል ይህን የመስላል። የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት ’መአህድ’ ኢህአዴግ በካድሬዎቹ አማካኝነት በአማራው ላይ የሚያካሂደውን የእልቂትና የሽብር ዘመቻ እያፋፋመው የአማራ ህዝብም ከፋሽስቶች ዘመን በባሰ ሁኔታ እያለቀ መሆኑን ባወጣው የአቋም መግለጫ አብራርቷል። የመአህድ ፕሬዜዳንት ለሽግግር መንግስቱ ምክር ቤትና ለልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ባቀረቡት መግለጫ ላይ እንዳብራሩት በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍና በደል ”ሰብአዊ አእምሮ ሊሸከመው የማይችል ነው” በተለይ ከግንቦት 26 ቀን 1984 ዓም ጀምሮ ጭፍጨፋው በከፋ መልኩ እንዲቀጥል ተደርጎ የጭፍጨፋው ሰለባ የሆነው አማራ ሬሳው በገደል ውስጥ እንዲጣልና በቤት ውስጥ እንዲቃጠል እየተደረገ ነው። ይላል

                       Pro Mesfin

”ከግንቦት 26 ቀን 1984 ዓም ጀምሮ በአማራው ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ የተካሄደው በአርሲ ክፍለ ሀገር በአንቦሳ ከተማና በአካባቢው ነው። ኢህአዴግ በዚህ ስፍራ የሚኖሩ ተወላጆችን ሰብስቦ ’በነዚህ መንደሮች የሚኖሩ አማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙ’ በማለት ትእዛዝ ሰጠ። በማግስቱ ግንቦት 27 ቀን 1984 ዓም አቡሌ የተባለውን መንደር በኦህዴድ (የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራቲክ ድርጅት) የታጠቀ ወታደር ተከቦ ተኩስ ከተከፈተ በሗላ መንደሩ በላውንቸር መደብደብና ማቃጠል ሲጀመር ህዝቡ ህይወቱን ለማዳን ህዝቡ በየአቅጧጫው መሸሽ ጀመረ። ከሚሸሹት መካከል 30 ህጻናት ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ እንደተጠጉ ከቤተክርስቲያኑና ከካህናቱ ጋር ተቃጥለዋል። አከታትሎም 150 የአማራ ነዋሪ ቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓል። የአውራጃው የኢህአዴግ ተወካይ አቶ ዲማ ጎርሜሳ ለወራሪው ሰራዊት ”አማራን መጨረስ ዛሬ ነው” የሚል መፈክር በማሰማት አበሳ የሚባለው የአማሮች መንደር እንዲከበብ አስደርገው ህዝብ ከቤቱ ሳይወጣ መንደሩ እንዲቃጠል ተደርገ። በመንደሩ ከነህይወታቸው በቤት ውስጥ እንዳሉ የሞቱት ቁጥር የማይታወቅ ሲሆን የቤቶቹ ጠቅላላ ብዛት 150 ነው። ከቃጠሎው የተረፉት 50 ሰዎች ተይዘው በጥይት ተረሽነዋል። በሌላም አሼ በተባለ መንደር በአማራ ተወላጆች በአካባቢው የሚፈጸመውን ሰቆቃ እየተመለከቱ የመንግስት ሃይል ያድነናል ብለው ሲጠብቁ 25 ሰዎች የኢህአዴግ ሰራዊት ፈጅቷቸዋል። በጉና ወረዳ አዲስ አለም በተባለ ቦታም 150 ቤቶችን ከነነዋሪዎቹ ከማቃጠላቸውም ሌላ ሁለት የአገር ሽማግሌዎች እጅ እግራቸውን አስረው አቃጥለዋቸዋል። ዋቄንትራ ከተባለው መንደር 100 ቤቶችን ከነነዋሪዎቹ አቃጥለዋቸዋል። መሶ የተባለውን መንደር በጦር እንዲከበቡና 100 ቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓ ከቃጠሎው የዳኑት 80 ሰዎች እጃቸው ታስሮ በኦህዴድ (የኢህአዴግ አንዱ ክፍል) ተረሽነው ሬሳቸው ቆሬ ከሚባል ገደል ውስጥ እንዲጣል ተደርጓል። አንድ ሰው በተአምር ከዚህ መአት ተርፏል። እንደሴ ባዩ የሚባለው መንደር ነዋሪ የሆኑ አማሮች በተመሳሳይ ሁኔታ በኦህዴድ ሰራዊት እነዲከበቡ ከተደረገ በሗላ ከመንደሩ ነዋሪዎች መካከል 80 የሚሆኑት እጅ እግራቸውን ታስረው ተወስደዋል። ወደ ገደል እንደተወረወሩም ይወራል። ስድስት ቤተ-ክርሲቲያናት በዚህ አካባቢ ተቃጥለዋል። ይህ ሁሉ የተፈጸመው ግንቦት 27 ቀን 1984 ዓም በአንድ ቀን ነው ሲል የመአህድ መግለጫ አብራርቷል። እንግዲህ ፕሮፌሰር መስፍን በሸገር ራዲዮ ጣቢያ የካዱት ይሄንን በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው።

moweswe@gmail.com

ምንጭ:

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35678

ጄነራል ከማል ገልቹ ከኦነግ መሪነታቸው ተነሱ

ጄነራል ከማል ገልቹ ከኦነግ መሪነታቸው ባላቸው የብቃት ማነስና በአምባገንነት ድርጊታቸው ከስልጣናቸው መነሳታቸውን ኢትዮ ሚዲያ ዘገበ።

ዝርዝሩን ከታች ይመልከቱ

አሜጋ ነኝ

Gen. Kemal Gelchu removed as OLF chairman
Ethiomedia
October 24, 2014

WASHINGTON, DC – The Oromo Liberation Front (OLF) said on Thursday its chairman, General Kemal Gelchu, has been relieved of his post and removed from the organization because of “poor leadership qualities and dictatorial actions.”

“General Kamal Galchu…has lost the moral and legal ground to continue to lead our organization. Allowing him to continue with his dictatorial actions will destroy an organization, thousands, if not millions have lost their lives and are still losing to maintain. His lack of leadership skills has been a complete abomination. He has lost the trust, confidence and respect of the organization, both as a leader and a person,” the executive committee of OLF which passed the decision said in a press release sent to Ethiomedia on Thursday.

OLF poured accusations over the former Ethiopian army general who fled to Eritrea in 2006 – taking with him a splinter regiment of 150 heavily armed soldiers. He has since then lived in Eritrea, where OLF maintains its headquarters as well as rebel base.

Oromo organizations in North America have over the years invited Gen. Kemal to appear as a guest speaker but he never left Eritrea, substantiating fears that the Eritrean regime has indeed placed the now-deposed OLF chairman under house arrest.

Ethiomedia’s repeated calls to General Kemal were not answered. To read OLF’s press release, click here.

ምንጭ:

http://www.ethiomedia.com/15store/4213 

በሃገር ቤት ላላችሁ ታዳሚዎቼ በሙሉ

ሰበር ዜና፣ ህውሃት “የመለስ ትሩፋቶች” መጽሃፍን ለስለላ እየተጠቀመበት መሆኑ ታወቀ

መረጃው የአባይ ሚዲያ ነው

አሜጋ ነኝ

ሰበር ዜና፣ ህውሃት “የመለስ ትሩፋቶች” መጽሃፍን ለስለላ እየተጠቀመበት መሆኑ ታወቀ

አባይ ሚድያ/ ጥቅምት 2፣ 2007

በቀድሞው የመንግስት ኮሚውንከሽን ጉዳዮች ሚንስትር ድኤታ አቶ ኤርምያስ ለገሰ የተጻፈውን እና በብዙ በአለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተነባቢ የሆነው “የመለስ ትሩፋቶች” የተስኘው መጽሃፍ የኢህአዴግን መንግስት በተለይም ደግሞ የህውሃትን የጥፋት ዘመቻ በሰፊው  ያጋለጠ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም መጽሃፉ ወደ PDF File  ተቀይሮ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ በኢሜይል ሲሰራጭ ቆይቷል።

መጽሃፉ በተለይ በዲሞክራሲ አክቲቪስቶች ዘንድ ተፈለኣጊነት እንደሚኖረው በማወቅ

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የደህንነት ምንጮቻችን በዛሬው እለት እንዳስረዱን የህውሃት ኢህአዴግ የስለላ ማእከል ይህንን ፋይል ፊን ፊሸር ከተባለ የስለላ ቫይረስ ጋር በማጣመር በአሁኑ ሰአት በከፍተኛ ፍጥነት በኢሜይል በማሰራጨት ላይ ይገኛል።

ይህ ቫይረስ ከ“የመለስ ትሩፋቶች” ፍይል ጋር ተጣብቆ ወደ ኮምፒውተር ዳውንሎድ ከተደረገ፣ ኮምፒውተሮት ላይ ያለውን የግል ፍይሎች ወድ ህውሃት የስለላ ማእከል ከመላክ እልፎ  የሚከተሉትን ማድረግ ይችላል፥

1)  የህውሃት ይስለላ ኤጀንቶች በኮምፒውተሮት ላይ ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ያደርጋል

2)  ይህ ማለት በፈለጉት ሰዕት የኮምፒውተሮትን ካሜራ እና ማይክሮፎን በመጠቀም የግል እንቅስቃሴዎን መከታተል እንዲችሉ ያደርጋል

3) በኮምፒውተሮት ላይ በኢንተርኔት  የሚስገቧቸውን እንደ ክሬዲት ካርድ እና ሶሻል ሴኵሪቲ ያሉ ሚስጥራዊ ቁጥሮችን  በቀላሉ ማግኘት ያስችላቸዋል

4) በኢንተርኔት ላይ የሚጎበኟቸውን ድረ ገጾች እንዲሁም  በግልዎ የሚሳተፉባቸውን የማህበርዊ ሚድያ አካውንቶች እስከ ዩዘር ስም እና ፓስዎርዳቸው በቀላሉ ማግኘት ያስችላቸዋል

5)  ከቤተሰብዎ እና ከጏደኞችዎ ጋር የሚያደርጉትን የኢሜይል እና የስካይፒ ግንኙነት በቀላሉ ማንበብ እና ማዳመጥ እንዲሁም አካውንቶቹን ሌላ ጥቅም ላይ ማዋል ያስችላቸዋል

6)  በድርጅት ውስጥም ሆነ በግልዎ ለስብአዊ መብትዎ ወይም ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የሚሟገቱ ከሆነ፣ እርስዎን በሃሰት ወንጅሎ ለእስር አና ለስቃይ ለመዳረገ መንገድ ይከፍትላቸዋል

ስለዚህ ይህ “የመለስ ትሩፋቶች” የሚል የPDF ፍይል በኢሜይል ከተላከልዎ የኢሜይል መልእክቱን ሳይከፍቱ ዲሊት በማድረግ እራስዎን ከጥቃት ያድኑ።

ምንጭ:

http://abbaymedia.com/amharic/2014/10/22/ሰበር-ዜና፣-ህውሃት-የመለስ-ትሩፋቶች/

BBC World reported about Zone 9 Bloggers

c177e-zone92bfractial2belement

In Ethiopia, a group known as the Zone 9 Bloggers are still awaiting trial several months after their arrest. The bloggers have been charged with associating with terrorists – a charge they deny. Critics say, in the lead up to next year’s general election, the government is clamping down on dissent and has made an example of the bloggers. Click hears from the Ethiopian government, from the Committee to Protect Journalists and from the co-founder of Zone 9 bloggers, Endalk Chala.

There are around 7,000 languages spoken on the planet today, and many of these are at risk, with a real fear that in the future we may lose many of them if they’re not used. In New Zealand, remote sensor technology and a powerful algorithm are helping save the iconic flightless bird the Kiwi. Click’s Simon Morton reports that the same home-grown technology is now being used to preserve New Zealand’s indigenous language, Maori

Post Gamergate how can tech companies and social media platforms use better algorithms to curb the exploitation of trolls to use social media to promote hateful and bullying campaigns? Click hears from the technology journalist , Natasha Lomas.

Fiducial Voice Beacons by Rafael Lozano-Hemmer is a sound art installation that consists of 40 interactive light beacons located on the ceiling of the Information Age gallery – a new gallery about to open in London’s Science Museum. Each beacon also holds a sound recording which is represented by glimmering beams of light that gently illuminate the gallery. Rafael Hemmer joins Click to demonstrate the technology that fuses the voices of punters with voices from past communication pioneers.

Photo: The founding members of Zone9 blogging collective, 4 December 2012. Credit: Endalk Chala

Source:

http://www.bbc.co.uk/programmes/p028n6d4

“አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል” – ታማኝ በየነ

“ከንግግራችን የማስታውሰው እኔ እዚህ ሆኜ በስልክ ብቻ ከምከታተል ልምጣ እያልኩት ነበር። እሱ ደግሞ በዚህ ደረጃ መምጣት የለብህም እዛው ብትሆን ነው የምትጠቅመን እያለኝ ተነጋግረን እንደጨረስን ታሰረ።” ታማኝ በየነ

ዘሓበሻ የዘገበችውን እንደወረደ አቅርቤዋለሁ

አሜጋ ነኝ ከኖርዌይ

አሻራ፦ ጤና ይስጥልኝ አርቲስና አክቲቪስት ታማኝ በየነ፤ በቅድሚያ ስለ ጊዜህ በአንባቢያን ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። አቶ አንዳርጋቸውን ለምን ያህል ጊዜ ታውቃቸዋለህ ? እንዴትስ ትገልጻቸዋለህ?

andargacew ashara magazine cover page

ታማኝ፦ አንዳርጋቸውን የማውቀው ከምርጫ 97 ጀምሮ ነው።በምርጫ 97 ቅንጅትን ተቀላቅሎ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ማለት ነው። ያኔ መቼም ሁላችንም ልባችን የምርጫው እንቅስቃሴ ላይ ስለ ነበር በየእለቱ እየደወልን ሁኔታውን እንከታተል ነበር። እኔም ራሴ ሃገሬ ገብቼ እንደልቤ በነጻነት ለመኖር የምችልበት ጊዜ አሁን ነው ከሚል እምነት የመግባት እቅድ ነበረኝ። አንዳርጋቸውን የማውቀው እንግዲህ በዛ ግዜ በነበረን የስልክ ግንኙነት ነው። እስኪታሰር ድረስ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ከመታሰሩ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያናገረኝ እኔን ነበር። ከኔ ጋር አውርተን ስልክ እንደዘጋ ነው የታሰረው።

ከንግግራችን የማስታውሰው እኔ እዚህ ሆኜ በስልክ ብቻ ከምከታተል ልምጣ እያልኩት ነበር። እሱ ደግሞ በዚህ ደረጃ መምጣት የለብህም እዛው ብትሆን ነው የምትጠቅመን እያለኝ ተነጋግረን እንደጨረስን ታሰረ። ከዚያም ተፈቶ ወደ እንግሊዝ አገር ተመለሰ። በኋላም በቅንጅት ኢንተርናሽናል ተመርጦ ሲሰራ በስልክም በአካልም እንገናኝ ነበር። ከአንዳርጋቸው ጋር የነበረን ትውውቅ ይህን ይመስል ነበር፡፡

እንዴት ትገልጸዋለህ? ላልከኝ፦በጣም አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜና መንገድ ህልሙን ሊያሳካ የደከመ ሰው ነው!። በተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት የውጭውን ዓለም ዘመናዊ ህይወት የለመዱ ከአውሮፓና ከአሜሪካ እየሄዱ የኢህአፓን ትግል ተቀላቅለው በርሃ የቀሩ ወጣቶች እንደነበሩ አንብቢያለሁ። በንባብ የምታውቀውን ታሪክ በአካል የምታውቀው ሰው ሲያደርግ ስታይ ደግሞ በጣም ከባድ ነው። በአውሮፓና አሜሪካ ህይወት ፤ ምግብ፤ አልባሳት፤መኝታ፤ መዝናኛ፤

ብቻ እያንዳንዷን ነገር በምርጫና በፍላጎት የምታደርግበትን ህይወት ለምደህ በርሃ ገብተህ፤ ድንጋይ ለመንተራስ፤ አሸዋ ለመልበስ፤ ላለመታጠብና ያልታጠበ ለመልበስ መወሰን እጅግ በጣም ከባድ ነው። አስበው ከእንግሊዝ አገር ከንግስቲቷ ከተማ ሄዶ አሸዋ ላይ መተኛት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ!።

ባጠቃላይ አንዳርጋቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ከራሱ ህይወት አልፎ ቤተሰቡ የከፈለውን መስዋዕትነት ሳይ የሚሰማኝ ስሜት ሃዘን ሳይሆን ይህን ሥርዓት በተለያየ መልኩ እንታገላለን ለምንል ወገኖች ትልቅ ምሳሌና አርአያ የሆነ ሰው መሆኑን ነው።

አሻራ፦ የወያኔ መንግስት አንድን ግለሰብ ለመያዝ ይህን ያህል ተጨንቆና ተጠቦ፤ ቀደም ሲል የግድያ ሙከራ ማድረጉ አሁን ደግሞ ከፍተኛ ወጪ አፍስሶ፤ ሁለተኛ አገር(የመን) የተሳተፈችበት ድንበር ዘለል አፈና መፈጸሙ ምን የፖለቲካ ፋይዳ አገኝበታለሁ ብሎ ይመስልሃል?

ታማኝ፦ በመጀመሪያ የአንዳርጋቸውን የዓላማ ጽናት (ኮሚትመንት) አብሯቸው በሰራ ጊዜ አይተውታል። ያውቁታል። ከወጣትነት ዕድሜው ጀምሮ በኢ.ህ.አ.ፓ በኋላም ከነሱ ጋር ሲሰራ ለራሴ የሚል ሰው እንዳልሆነ፤ ስልጣን ይዞ ለመንደላቀቅ፤ ቤት ለመስራት፤ መኪና … የመሳሰሉት ቁሳዊ ፍላጎት የሌለው ሰው እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል። የአንዳርጋቸው የዘወትር ቁጭት ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ብዙ ያልተሟሉ ጉዳዮች ስላሏት እነሱን ለማሟላት መሆኑንም ያውቃሉ። ከቅርብ ጊዜው ብናይ እንኳ በምርጫ 97 ቅንጅትን ተቀላቅሎ በአጭር ግዜ ውስጥ ምን ያህል ህዝብን የማሰባሰብና የማደራጀት ስራ እንደሰራ እናስታውሳለን።

ባለፈው አስመራ ድረስ ቅጥር ነፈሰ ገዳይ ልከው ሊያስገድሉት መሞከራቸውን ኢሳት በዘገበበት ጊዜ እንዴት ሊሆን ይችላል?ይሄ የኢሳት ወሬ ነው ያሉኝ ሰዎች ነበሩ። እነሱ(ወያኔዎች) ግን በየት በኩል ጉዳት ሊመጣ እንደሚችል በደንብ ገብቷቸዋል።በኔ ግንዛ አንዳርጋቸው የማስተባበሩን ስራ ጥሩ አድርጎ እንደሚሰራ ስላወቁ ይመስለኛል ይህን ያህል ክትትል አድርገው ሊይዙት የቻሉት።
Tamagn

አሻራ፦ እንዳልከው አቶ አንዳርጋቸውን መያዝ ማለት የተቃዋሚውን አከርካሪ እንደመስበር ሳይቆጥሩት የቀሩ አይመስልም።ይሁንና አቶ አንዳርጋቸውን የመን ላይ ይዘው መውሰዳቸው ለግዜው ጮቤ ቢያስረግጣቸውም፤ ውጤቱ ግን “ አሳ ጎርጓሪ….” ሆኖባቸዋል የሚሉ ብዙ ናቸው፡፡ አንተስ በዚህ ሃሳብ ትስማማለህ?

ታማኝ፦ በጣም እንጂ የምስማማው።እኔ እንግዲህ ህወሃት አገሪቷን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ በተቃዋሚነት አብሬ ኖርያለሁ። በውጭው ዓለምም አውሮፓ ፤ አውስትራሊያ ፤ አሜሪካ …ያለውን የተቃዋሚውን ወገን እንቅስቃሴ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አውቃለሁ እላለሁ። እናም ከቅንጅት በኋላ “የምን ፖለቲካ?…ፖለቲካ በቃኝ!” እያለ የሸሸው ሰው ሁሉ በፈቃደኝነት “ምን እናድርግ?” ብሎ የመጣበት ወቅት ነው አሁን።

የአንዳርጋቸውን ነገር የተለየ የሚያደርገው ደግሞ፦ አንዳርጋቸው በየመድረኩ የሚታይ ሰው አይደለም። ከሱ በበለጠ እኔ በብዙ መድረክ እታያለሁ።

እሱ ግን የሚሰራ እንጂ የሚታይ ሰው አልነበረም፡፡ ይሁንና ህውሃት ይህን ያህል ሊያጠፋው የፈለገው አንዳርጋቸው ምን አይነት ሰው ቢሆን ነው? የሚለውን ነገር እንድት ጠይቅና እንድታገናዝብ ያደርግሃል። ለዚህም ይመስለኛል በውጭም በሃገር ቤትም የሚገኘው ህዝብ በሚያስደንቅ መልክ የተንቀሳቀሰው።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር ጋር ስንወያይ “በታሪክ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ለለውጥ ምክንያት ይሆናሉ” ነበር ያለኝ። እኔም አንዳርጋቸው የለውጥ ምክንያት እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። በርግጥ በዚህ መልክ መሆኑና እየደረሰበት ያለውን ስቃይ ስታስብ ቢያምህም በህዝብ ውስጥ የፈጠረው የመተሳሰብና የአብሮነት ስሜት ግን ቀላል አይደለም። ፊት ለፊት የማይተያዩና መነጋገር የማይፈልጉ ተቃዋሚዎች ያወጡትን ተመሳሳይ ቁጭት፤ እልህና ንዴት የተንጸባረቀበትን መግለጫ ስታየው ህወሃቶች እራሳቸው ምነው በቀረብን ሳይሉ የሚቀሩ አይመስለኝም። አንዳርጋቸውን መያዛቸው በርግጥም “አሳ ጎርጓሪ..” ሆኖባቸዋል በሚለው ሃሳብ እስማማለሁ።

አሻራ፦ አሁን ደግሞ በቅርቡ ለእይታ ወዳቀረብከው “ተላላኪው ማነው?” ወደሚለው የምስል ዘገባ ልመልስህ፦ ይህን ስራ ለማቅረብ ምክንያት የሆነህ ወይም መነሻ ሃሳቡን ያጫረብህ ጉዳይ ምንድነው?

ታማኝ፦ እእ …! ሁሌም በአይምሮዬ የሚመላለሱ ጥያቄዎች አሉ፦ የህወሃት መሪዎች ከሟቹ ጠ/ሚንስትራቸው ጀምሮ “እነዚህ የሻቢያ ተላላኪዎች” የሚሉት ነገር አለ። እናም ሁሌ እነኝህ ሰዎች እውነት ሰው አያውቅብንም ብለው ያስባሉ? እያልኩ እራሴን እጠይቃለሁ። አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር “እነኚህ የሻቢያ ….” ሲሉ እየቀለዱ ነው? እላለሁ።

አሁን ደግሞ አንዳርጋቸውን ከያዙ በኋላ ይህንኑ አባባላቸውን ደጋግመው ሲጠቀሙበት …. አልበዛም? የሚል ስሜትና የነሱ መሬት የለቀቀ ውሸት ነው ለሥራው ያነሳሳኝ።

አሻራ፦ አቶ አንዳርጋቸውን ለሁለተኛ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮ ያቀረቧቸው “ተላላኪው ማነው?” የሚለው የታማኝ የምስል-ዘገባ በኢሳት እንደሚቀርብ ከማስታወቂያው በማወቃቸው ሳይቀደሙ ለመቅደም አስበው ነው ሲሉ ብዙዎች አስተያየት ሰንዝረዋል። በተለይ ያቀረቡት የፊልም ዘገባ የሚጀምረው “የሻቢያ ተላላኪዎች” በሚሉ ቃላት መሆኑ የአስተያየቱን ትክክለኝነት ያጎላዋል ይላሉ…በዚህ መልክ ታይቶሃል?

ታማኝ፦ እንዳልከው የተሰነዘሩ አስተያየቶችን ሰምቻለሁ። ምንድነው ከባዱ ነገር መሰለህ ? የኔ ስራ ከመውጣቱ በፊት ለመቅደም ሲሉ አዘጋጁት ብል የኔ ከፍታ ሊጨምር ነው፤ መንጠራራት ሊሆንብኝ ነው። ከኔጋ እየተከራከሩ ነው ማለት በጣም በጣም ይከብዳል። ከተለያዩ ሰዎች የተሰነዘሩ አስተያየቶችን ስትመለከት፤ የቪዲዮው ያለ ጥንቃቄ ተከታትፎ (በአግባቡ ኤዲት ሳይደረግ) በችኮላ መቅረብ፤ የተጠቀሙበት ቃልና ከኔ ሥራ ጋር በአንድ ቀን መልቀቃቸው እነኚህን ነገሮች እንድታስብ ያደርግሃል። ጥድፊያቸው ደግሞ ከአንዳርጋቸው ቃል ጀርባ ያለውን የጣር ድምጽ እንድንሰማ እስከማድረግ ያደረሳቸው ነው። ይህን ይህን ደማምረህ ስታይ አንተ ከምትለው ጋር ይቀራረባል ። እኔ ግን ለኔ መልስ ሰጡ ብዬ ማለት ይከብደኛል።

አሻራ፦ እንደ መንግስት አስበሃቸው ይሆን ለኔ መልስ እየሰጡኝ ነው ማለት ይከብደኛል ያልከው?

ታማኝ፦ በጭራሽ!! እንደ መንግስት ቢያስቡና እኔም እንደ መንግስት ባስባቸውማ በወደድኩ ነበር። ዋናው ችግር እንደ መንግስት አለማሰባቸው ፤ እንደ መንግስት አለመስራታቸው አይደል እንዴ?እንዴት አድርጌ ነው እንደ መንግስት የማስባቸው? እኔ ይህን የምለው ሕዝብን ከማክበር ነው። በግለሰብ ደረጃ የሰጠሁት አስተያየት ወይም ያቀረብኩት ስራ ሊታይ የሚገባው በዛው ደረጃ መሆኑን ስለማምንበትና ከዛ በራቀ እንዳይታይብኝ ነው።
Fezralizm – By Tamagn Beyene Part 2
አሻራ፦ በቅርቡ በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አወያይነት አንተ፤ አቶ ኤርሚያስ ለገሰና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ወንድማገኝ ጋሹ በኢሳት ቀርባችሁ ባደረጋችሁት ውይይት ብዙዎችን ያስገረመ ነገር አስደምጠሃል። ያስደመጥከው ነገር፦ ጥቂት የወያኔ ባለስልጣናት በተገኙበት ውይይት ላይ አቶ በረከትና አቶ አዲሱ የተናገሩትን ነው። ይህ ውይይት በኢሳት መደመጡ ተቃዋሚው ወያኔ ጉያ ውስጥ ለመግባቱ አመላካች ሆኗል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ትግሉ የደረሰበትን ደረጃም ያሳያል የሚሉም አሉ፡፡ እንደ ጥያቄ ማንሳት የምሻው ይህን አይነት ጥብቅ ሚስጥር ኢሳት እጅ ሊገባ መቻሉ የተቃዋሚው የመረጃ ክፍል ጥንካሬ ወይስ ወያኔ ውስጡ ከመቦርቦሩ ጋር በተገናኘ እየሆነ ያለ …?

ታማኝ፦ ህዝቡ እኮ ታፍኖ የመጨረሻ ግፍ እየተቀበለ ነው ያለው። ደርግ ክፉ ነገሮችን ሁሉ ጨርሶ አድርጓቸው ሄዷል፤ ከደርግ በላይ ማንም ምንም አይነት ግፍ ሊፈጽም አይችልም የሚል እምነት ነበርን፡፡ እነዚህ ግን እኮ ሁሌም የሚሰሩት ግፍና ክፋት እያስደነቀን ነው።

ክፋታቸውን ቢያሳይ አንድ ምሳሌ ልንገርህ፦ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ቀርበው በነበረበት ጊዜ፤ በርሃብ ምክንያት መናገር እንኳ አቅቷቸው፤ ለዳኛው ምግብ በልተን አናውቅም ብለው ሲናገሩ፤ ዳኛው ደንግጦ ምግብ አምጡላቸው ብሎ ፍርድ ቤት ውስጥ እኮ ምግብ ተበላ! እነኚህ ሰዎች እኮ ያሰሩትን ሰው በርሃብ የሚቀጡ ናቸው ! እረ ስንቱን…… ዘርዝሬ እችለዋለሁ?

የህዝብን ስሜት በጥቂቱም ሊያሳይ ከቻለ አንድ ነገር ልንገርህ፦ በቅርቡ ለኢሳት አራተኛ አመት ወደ ጀርመን ሄጄ ነበር፡፡ በዝግጅቱ ላይ አንድ ሰው እጁን አውጥቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር፡፡ በክፍለ ሃገር ቤተሰቤ በሚገኝበት አካባቢ ለሚኖሩ አንድ አዛውንት ለቡና መግዣ ብዬ 50 ዩሮ ሰጠኋቸው። ተቀብለው ካመሰገኑኝ በኋላ፤ ሰማህ ወይ ልጄ ከዚህች 50 ብር ላይ ዘርዝርና 10 ብሩን ለዛ ለታማኝ በእጁ ስጥልኝ፤ ለኢሳት ገቢ እንዲያረግልኝ ብለው ሰጥተውኛል።” ነበር ያለው፡፡ ተመልከት በዚህ አይነት የኑሮ ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያዊ እንኳ ከተሰጣቸው 50 ዩሮ 10 ለኢሳት ይሰጥልኝ አሉ።ይሄ እኮ ሌላ ምንም ማለት አይደለም። ህዝቡ ምን ያህል ነጻነት እንደናፈቀ የሚያሳይ ነው። የሰውን ፍላጎት ነው የምነግርህ፡፡

በመረጃ በኩልም ህዝቡ ለትግሉ የሚጠቅም መረጃ ለመላክ በሚገርም መልኩ ፍቃዱና ፍላጎቱ አለው። ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ ሳይፈራና መስዋዕትነት ከፍሎም ቢሆን መረጃዎችን ለመላክ ይፈልጋል።

ኢሳት አሁን አብዛኛውን መረጃ የሚያገኘው ከህዝብ ነው። እኔ በግለሰብ ደረጃ ነው መረጃዎቹ የሚደርሱኝ፡፡ አንድ ጠንካራ ድርጅት ተፈጥሮ በዚህ ረገድ ስራ ቢሰራ ደግሞ ምን ያህል እንደሚተባበር መገመት ከባድ አይሆንም።

አሻራ፦ ወደ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልመልስህ፦ አቶ አንዳርጋቸው ላይ አፈናው በተፈጸመበት ሰሞን በለንደን በተደረገ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተህ በነበረበት ወቅት አቶ አንዳርጋቸው የአንበሳ ምስል በልዩ ሽልማት መልክ ሲሰጡህ ከሚያሳይ ክሊፕ ጋርአዳብለህ “ አንዳርጋቸው አንበሳውን መልሰህ ተቀበለኝ፤ ለኔ አይገባኝም!” የሚል መልዕክት አስተላልፈሃል። ይህን ያዩ ሰዎች ለአንድ ሃገር አንድ አንበሳ ብቻ ነው የሚያስፈልጋት እስካልተባለ ድረስ ታማኝም አንዳርጋቸውም ለሃገራችን አንበሶች ናቸውና ታማኝ ለምን ያንን አደረገ? ሲሉ ይጠይቃሉ። በርግጥ ለአቶ አንዳርጋቸው ያለህን ክብር ለመግለጽ የተጠቀምክበትን አገላለጽ ብዙዎች ወደውታል ። እስቲ ይህን ልትል ያስቻለህን …. ግለጽልን፡፡

ታማኝ፦ ያንን ያልኩት በስሜታዊነት ወይም በግብታዊነት አይደለም። ከልቤ የተሰማኝንና የሚሰማኝን ነው የተናገርኩት። አንዳርጋቸው አንበሳውን ለኔ ሲሸልም ስለኔ የተናገረው ራሱ በጊዜውም ከብዶኛል። እኔ ቀደም ሲል እንደ ገለጽኩልህ ራሴን የማየው እንደ አንድ ለህዝብ ነጻነትና ለሃገሩ ሰላም ፤ ….የሚናፍቅ ዜጋ ነው። አንዳርጋቸው በዚህ እድሜው ለህዝቡና ለሃገሩ ሲል የወሰደው እርምጃ በጣም ያስደንቀኛል። ሊከፍል የተዘጋጀው መስዋእትነት ሳያንስ እንደገና አፈናው ሲፈጸምበት ልንላቸው ይገባል፡፡

እነሱ (ገዢው ፓርቲ) በፍርሃት ዓለም ውስጥ ስለሆኑ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ነው ሩጫቸው፡፡ ወደፊት መቼም ቻይና የማትሰራው ነገር የለምና አገር ስትገባ ኤርፖርት ላይ ለመንግስት ክፉ -ልብ ያለውን ስካን የሚያደርግ መሳሪያ ሁሉ ሊያሰሩ ይችላሉ ….(ሳቅ)። ምርጫውንም ቢሆን ከዚህ በተለየ አይደለም የማየው። ፍርሃት ውስጥ ያለ አካል እውር ድንብሩን ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል።

አሻራ፦ አንዳንድ ሰዎች ታማኝ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን የራራላቸው ይመስላል። አቶ መለስን የተነፈሷትን ቃል ተከትሎ ወዲህ ወዲያ ያደርጋቸው እንዳልነበር ለአቶ ሃይለማሪያም ምነው ዝም አለ ይላሉ?

ታማኝ፦ ሳቅ…………! ይህን የሚሉ ሰዎች እውነት ከልባቸው እኔ በአቶ ኃይለማሪያም ላይ ግዜ እንዳጠፋ ፈልገው ነው? አይመስለኝም፡፡ አቶ መለስ እኮ የራሳቸው ተረት ፤የራሳቸው ስድብ ፤የራሳቸው፤ ውሸት የራሳቸው ምናምን…የነበራችው ሰው ነበሩ። አቶ ኃይለማሪያም ደግሞ ሳይዛቸው አልሆን ብሎ እንጂ የአቶ መለስን ልብስ ሊለብሱ የሚፈልጉ ነው የሚመስለኝ።

የአገር መሪዎች ከስራ ውጭ መጽሄት ማገለባበጥ፤ የአለም ዜና መከታተል …. እንዲህ እንዲህ አይነት ነገር እደሚያደርጉ ነው የማስበው፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ግን ሌሊት ሁሉ ቁጭ ብለው የአቶ መለስን ቪዲዮ የሚያዩ ነው የሚመስለኝ፡፡ “ እስኪ የ 94ቱን አምጪልኝ የ93ቱን ጨርሻለሁ እያሉ…” እና በእኝህ ሰው ላይ ነው ግዜ እንዳጠፋ የሚፈለገው? ለሳቸው የሚሆን ግዜ እንኳ የለኝም፡፡ በቁምነገር ልወስዳቸው አለመፈለጌ እንጂ አቶ ኃይለማሪያም እንዴት ያለ ኮሜዲ ሊሰራባቸው የሚችሉ መሰሉህ?

አንተ ኮ! ስትኮርጅ የሰውን ሃሳብ፤ ወይም ሻል ያለ ነገር ትኮርጃለህ ። ማዛጋት ትኮርጃለህ?…..(ሳቅ) እሳቸው እኮ የአቶ መለስን ማዛጋት ሁሉ እየኮረጁ ነው! (ሳቅ)……! እኔ እንደ መዝናኛና ኮሜዲ ሾው ነው የማያቸው። ከዚህ ባለፈ አላያቸውም። አይ የግድ ይሰራባቸው ከተባለም ለቁምነገር ሳይሆን ለትርፍ ግዜ መዝናኛ ሊሰራባቸው ይችላል፡፡ከዚያ ውጭ ግን በሳቸው ላይ ግዜ ማጥፋት ያለብኝም ያለብንም አይመስለኝም።

ደግሞ ምን መሰለህ..? እኔ ጠ/ሚ/ር ስትለኝ የሚመጣብኝ ምስል እንደ አክሊሉ ሃብተወልድ አይነት ሰው ነው፡፡ ….እና በዚህ ስም ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሲጠራበት ……(ፋታ) ልክ አይሆንም፡፡

አሻራ፦ የወያኔን ከፍተኛ ባለስልጣናት በስልክም ቢሆን ለማግኘት ሞክረህ አታውቅም? ሞክረህ ከሆነ ውጤቱ ምን ነበር?

ታማኝ፦ እምምም.. አዎ! አንድ ሶስት ግዜ ሞክርያለሁ፡፡ አንዴ የቤንሻንጉል መፈናቀል ጊዜ …ሌላው ደግሞ አርሲ ውስጥ ሙስሊሞች የተገደሉ ጊዜ ይመስለኛል…አንዱን ዘነጋሁት። ብቻ ለ3 ጊዜ ያህል አቶ በረከት ጋ ደውዬ ነበር።መጀመሪያ የደወልኩ ጊዜ አነሳ፤ ጤና ይስጥልኝ ከአሜሪካ ነው የምደውለው አልኩት። “ማን ልበል? ” አለኝ። አይ እኔ የመንግስትዎ ተቃዋሚ ነኝ፤ ነገር ግን አሁን እየሆነ ባለው ጉዳይ መረጃ ይሰጡኝ እንደሁ ብዬ ነው የደወልኩት አልኩት።

እሱም “ማንነትክን ካልገለጽክልኝ ምንም መረጃ መስጠትም ሆነ ማውራት አልችልም” አለኝ።

መልሼም፦ማንነቴን ከነገርኩዎት አያናግሩኝም አልኩት። “ግዴለህም አናግርሃለሁ!” አለኝ።

ታማኝ በየነ ብዬ ሳልጨርስ ስልኩ ላዬ ላይ ተዘጋ፡፡በሌላም ጊዜ የሆነው እንዲሁ ነው፡፡ ታማኝ በየነ ነኝ ስለው ስልኬን ይዘጋዋል።

አሻራ፦ ለማነጋገር ፈቃደኛ ቢሆን ኖሮ በምን አይነት ስሜት ነበር የምታናግረው? ምንስ ነበር የምታናግረው?

ታማኝ፦ ለነገሩ በተለይ በመጀመሪያ የደወልኩለት ጊዜ አልተዘጋጀሁም ነበር፡፡ አሁን ስልኩን ሲያነሳ እንዴት ብዬ ነው የማናግረው? ንዴትም ቁጣም ፤ እልህም ይኖራል እና እንዴት እንደማናግረው አላውቅም ነበር፡፡ ሰዎችም አብረውኝ ነበሩ። ለማንኛውም የምለውን ሳልል እሱም ስልኩን ዘጋው። ሁለተኛ ስደውል ግን አስቤበት ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው ስልኩ ይነሳና ራሴን ሳስተዋውቅ ይዘጋል።

አሻራ፦ ምን ትለው ነበር ?

ታማኝ፦ሁሌ ራሴን የምጠይቀውን ነገር ነበር ልጠይቀው የፈለኩት። እንደው መጨረሻችሁ ምንድነው? እውነት እናንተ ሰዎች የምታደርጉትን ነገር ሁሉ የምታደርጉት የምር!! ለሃገርና ለህዝብ ጥሩ እየሰራን ነው ብላችሁ አምናችሁበት ነው? ልጆቻችሁን ትወዳላችሁ? ልጆቻችሁ ከሌሎች ልጆች ጋር በፍቅር እዲኖሩ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ብዬ ጠይቄ ከራሳቸው አንደበት ብሰማው ፈልጌ ነበር አልሆነም ዘጋብኝ፡፡

አሻራ፦ ወደ ወቅቱ ጉዳይ ልመልስህ፦ የአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ኢትዮጵያዊውን ሁሉ አስቆጥቷል፡፡ በወያኔ መንግስት ላይ ያለው ተቃውሞና ለለውጥ ያለው ተነሳሽነት ከመቼው ጊዜ በተለየ ጠንክሯል። ይህን ተነሳሽነት ወደ ውጤት ለመለወጥ ምን መደረግ አለበት ትላለህ?

ታማኝ፡- አንድ ነገር አለ! በአሁኑ ሰአት በሃገራችን እየሆነ ያለው ነገር በጣም የሚያስፈራ ነው፡፡ እኛ የምንቃወማቸው ስለምንጠላቸው አይደለም፡፡ የምንቃወማቸው እያደረጉ ያሉት ነገር በጣም የሚያስፈራ፤ ሃገራችን እንደ ሃገር ህልውና እንዳይኖራት፤ ህዝባችንም አብሮ መኖር እንዳይችል የሚያደርጉ ሥራዎችን እየሰሩ በመሆኑ ነው። በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተደጋጋሚ የዘር ቅራኔዎችን እያየን ነው። እገሌ ከዚህ ክልል እገሌ ከዚህ ክልል ውጣ እየተባለ ህዝብና ህዝብ እየተቂያቂያመ እንዲሄድ እየተደረገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ያስፈራል፡፡

የህክምና ባለሙያ ባልሆንም አንድ ዶክተር ወደ ካንሰር ሊለወጥ የሚችል በጣም ከባድ የጤና ችግር ያለበትን በሽተኛ ፡ በአግባቡ መርምሮ ዘለቄታዊ መፍትሄ ይፈልግለታል እንጂ ህመም አስታጋሽ (ፔይን ኪለር) የሚሰጠው አይመስለኝም፡፡ የሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። ዛሬ አንድ ዘላቂ መፍትሄ ነገር ካላደረግን ችግሩ ሊድን ወደማይችል ካንሰርነት መለወጡ አይቀርም።

ኢትዮጵያን ሃገሬ የምንላት ሁሉ አትሌቶቻችን ባንዲራዋን ለብሰው ትራክ ላይ ሲያሟሙቁ፤ ማን በ10 ሺህ ተሰለፈ ? ማን ለወርቅ ተስፋ አለው? …. እያልን እንጨነቃለን ። በውጤቱም እንደሰታለን። አሁን ደግሞ አትሌቶቿ ወርቅ ሲያስገኙላት የምንቦርቅላት ሃገር እንደ ሃገር መቀጠሏ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ይህ ደግሞ በኛና በኛ ትከሻ ላይ ብቻ ያረፈ ችግር ነው። ስለሆነም ከዚህ በፊት በተቃዋሚነት ሲንቀሳቀስ የቆየውም ሆነ ያልተንቀሳቀሰው ዜጋ፤ ብቻ ሁሉም ሁሉም ባመነበትና ታግሎ ያታግለኛል ባለው በአንዱ መስመር ገብቶ መታገል አለበት እላለሁ፡፡ ዛሬ አንዱ ተመልካች አንዱ ሯጭ የሚሆንበት ጊዜ አይደለም። ማንም ለምንም ጥሪ የሚያደርግበት ጊዜም አይደለም። ዛሬ አንድ ነገር ካላደረግን ለልጆቻችን የምናስተላልፈው “ነገ” የለም፡፡በዚህ ደረጃ ነው መታየት ያለበት የሚመስለኝ።

አሻራ፦ በተነሳንበት እንቋጭና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለህዝብ ነጻነት በጽናት ሲታገሉ ጠላት እጅ ወድቀዋል ፤ ህዝብስ ለሳቸውም ሆነ ለሃገር ነጻነት በመታገል ረገድ ምን ይጠበቅበታል ትላለህ?
Andargachew Tsige
ታማኝ፡- አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ እስከወደቀበት ጊዜ ድረስ የራሱንና የቤተሰቡን ህይወት ሰውቶ፤ በርሃ ገብቶ የቻለውን ሁሉ አድርጓል። የአንዳርጋቸው የትግል ጉዞ እዛ ጋ አብቅቷል። ዓለም ላይ ያሉ ሰውን የማስቃያ ቴክኒኮችን ሁሉ በእጁ ያስገባው የወያኔ መንግስት ደህንነት ባለፉት ሁለት ወራት አንዳርጋቸው ላይ ምን ሲፈጽምበት እንደቆየ ለመገመት የካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን ቃለ ምልልስ ማድመጡ በቂ ይመስለኛል፡፡ አንዳርጋቸው ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል። እየከፈለም ነው።

የወያኔ መንግስትን ባህሪ መለስ ብለን ብናይ ሕዝብ የሚያከ ብራቸውን ሰዎች አዋርዶና አቅልሎ ለማሳየት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡

በአቶ አንዳርጋቸው መታፈን የተቆጣውን ህዝብ ተስፋ ለማስቆረጥ በተለመደው መልክ አቶ አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል። ዋናው ቁምነገር ግን ህዝባችን ለዚህ መሰሉ የወያኔ ተደጋጋሚና አሰልቺ ህዝብን የማሳሳት፤ ጉምቱ የህዝብ ወኪሎችን የማዋረድ ሴራ አዲስ ስላልሆነ ምንም ይበሉ ምንም ይስሩ ፕሮፓጋንዳው ውጤት እንደማይኖረው አልጠራጠርም፡፡

ዋናው ቁም ነገር የነሱን ፕሮፓጋንዳ ማክሸፍ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት ስንታገልለት የቆየነው ዘረኛውን መንግስት ከሕዝብ ጭንቃ ላይ የማውረድ ዓላማ በውጤት እንዲቋጭ ሁላችንም አንድ ሆነን መነሳት ነው!!!።

አሻራ፡ ስለ ጊዜህ በድጋሚ እናመስግናለን! ታማኝ፡ እኔም ስለተሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ::

በአውስትራሊያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማስታወስ ከታተመችው አሻራ መጽሄት የተወሰደ::

ምንጭ:

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35593

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በቤተ ክህነት ውስጥ ሆነው የሚያምሱት እና ማኅበረ ቅዱሳን ላይ እጃቸውን የሚቀስሩቱ ለሃይማኖቱ ክብር ባለው በትግራይ ሕዝብ ታንቅረው የተተፉ ለመሆናቸው እማኝ የሆንኩባቸው አጋጣሚዎች (ከማስታወሻ ደብተሬ)

የዛሬ ስድስት ዓመት ገደማ ይመስለኛል በቀድሞ መስርያ ቤቴ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አብሮኝ ይሰራ የነበረ እና የመንፈሳዊ ወንድሜ የሆነ ወዳጄ ሰርጉ መቀሌ ላይ  ነበር።ሙሽሪት አባት እና እናቷ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ነበሩ።መቀሌን ከእዚህ በፊት ወደ አክሱም ፅዮን መንፈሳዊ ጉዞ  ስንሄድ መቀሌ ጊዮርጊስ ስናርፍ በማደር እንጂ በውል አላውቃትም ነበር።ከተማዋን ለእዚህ ወዳጀ ሰርግ በሄድኩበት ወቅት በቆየሁባቸው ሁለት ቀናት ውስጥ ግን  የአፄ ዮሐንስ ቤተ መንግስትን እና በመቀሌ የማኅበረ ቅዱሳን ማዕከል ፅህፈት ቤት ለማየት ዕድሉ ገጥሞች ነበር።መቀሌ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን ፅህፈት ቤት የነበሩት እና መቀሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ያሉ  ወንድሞች እና እህቶች ትሕትና እስከመቼም አይረሳኝም።

Aksum 1

በተለይ ወደ አክሱም ፅዮን በሁለት የተለያዩ ጊዜያት ከመንፈሳውያን ሰራተኞች ጋር ጉዞ በሄድንበት ወቅት አዳራችን መቀሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ነበር። የመቀሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ትምሕርት ቤት አባላት  ትህትና ከአዕምሮዬ አይጠፋም። በመንፈሳዊ ጉዞው የነበሩትን ከአንድ መቶ ሃያ የማያንሱትን መንገደኞች በሙሉ እግር አጥበው፣ለእያንዳንዳችን ነጠላ ጫማ እና ፍራሽ  ከቤታቸው ሰብስበው አምጥተው፣እራት አብልተው እና ለሚቀጥለው ቀን ጉዞ ስንቅ የሚሆነን እኛ ተኝተን እነርሱ ሌሊቱን ሲሰሩ አድረው የሚሸኙን እነኝሁ የመቀሌ መንፈሳውያን ወጣቶች ነበሩ።

ወደሰርጉ አጋጣሚ ልመልሳችሁ 
እድምተኞች በታደሙበት ሆቴል፣በሰርጉ ምሽት እራት ላይ ከአዲስ አበባ ድረስ አብረውን የሄዱት አባት ለሃያ ደቂቃዎች ያህል ትምህርት አስተምረው ሲጨርሱ ከታዳሚው አንድ ሰው ተነሱ እና በትግሪኛ መናገር ጀመሩ።እጅግ መቆጣታቸው በንግግራቸው መሃል እንባ እና ሳግ ሲተናነቃቸው ያስታውቃል።በመሃል ትግርኛውን ገታ አድርገው በሚጣፍጥ አማርኛ ቀጠሉ ከንግግራቸው መሃከል የማስታውሰው  ”ወንድሞቻችን እንደገባኝ  ከአዲስ አበባ ነው የመጣችሁት። የመቀሌ ህዝብም ተቸግሯል።አሰሙልን! ንገሩልን! ቤተ ክህነት ያሉት ሰዎች ምን እየሰሩ ነው? እየሾሙ የሚልኩት ላይ ጥያቄ አለን።ቅሬታ አለን ስንል ስም ይለጥፉብናል ።መናፍቅ እና ተሃድሶ ከቤተ ክህነት ይውጣልን!አያምታቱን! ንገሩልን! ሃይማኖታችን እየተዋረደች ነው” እጃቸውን እያወራጩ ነበር የሚናገሩት። የሰርጉ ታዳሚ በሃዘን ከንፈሩን መጠጠ።ሙሽራው እና አብረውን የሄዱት አባት ከአዲስ አበባ መምጣታቸው ብቻ ቤተ ክህነት የሚሰማቸው መስሏቸዋል።እኛ ከአዲስ አበባ መምጣታችን ብቻ ለቤተ ክህነት የቀረብን አድርገውናል።ቆይቶ የሙሽሪት ወላጅ እንዳስረዱን የተናገሩት አዛውንት የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሰብሳቢ በከተማዋም ውስጥ ከቀድሞ መንግስት ጀምሮ የታወቁ እና የተከበሩ አዛውንት መሆናቸው ነገሩን።

ተመሳሳይ ጉዳይ አክሱም ፅዮን አጋጥሞኛል። አክሱም ፅዮን ለመጀመርያ ጊዜ መንፈሳዊ ጉዞ ስሄድ ወደ ስልሳ የምንጠጋ  መንገደኞች በአንድ አውቶብስ ተሳፍረን ነበር  ከአዲስ አበባ የተነሳነው። አክሱም ፅዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያንን፣የአክሱም ሃውልት፣የቅዱስ ያሬድ ቃለ ሙራድ? የተቀበለበት ቦታ እና የንግሥት ሳባ ቤተ መንግስትን ያየሁበት አጋጣሚ ነበር።በአንድ መኪና የመጣው መንገደኛ በሙሉ የሚያድረው ከቤተክርስቲያኑ አጠገብ ከሚገኝ የእንግዶች ማረፍያ ጠበብ ያለ አዳራሽ ነበር።

በምሳ፣በእራት እና በቁርስ ሰዓት ለመንገደኞች ውሃ ማምጣት ኃላፊነት ከተሰጣቸው ውስጥ ነበርኩ። በመሆኑም በቀን ጊዜ ወደ አስር ደቂቃ የሚያስኬድ ሬስቱራንት መሄድ እና ውሃውን በባሊ ማምጣት ነበረብን። በእዚህ መሃል ነበር  ውሃ በነፃ እንድንወስድ የፈቀደልን የሬስቱራንት ባለቤት ጋር መግባባት የቻልነው።ግለሰቡ አዲስ አበባ የኖረ የአክሱም ሰው ነበር።በንግግራችን መሃል ታድያ ባብዛኛው የምናተኩረው በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ዙርያ ነበር።ግለሰቡ ከንግግሮቹ ሁሉ ጎልቶ የሚወጣው  የቤተ ክህነቱ  በሙሰኞች እና ከሃይማኖታዊ ምግባር እና ቀኖና በወጡ አገልጋዮች የበላይነት መመራቱ እንደሚያሳዝነው ነበር።ሁሉን ማውራቱ እዚህ ላይ ባይጠቅምም ከነገረን ውስጥ የሚገረመው ግን የአክሱም ከተማ ምዕመናን በቅርሳቸው ጥበቃ ላይ የሚፈሩት ከባዕዳን እኩል ቤተ ክህነቱ ውስጥ ያሉ እንደ እርሱ አጠራር ”ዘራፊ እና ቀማኛዎችን” መሆኑን ሲነግረን ሁላችንም በድንጋጤ የተያየንበት ወቅት ነበር።

እነኝህ ሁለት አጋጣሚዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በቤተ ክህነት ውስጥ ሆነው የሚያምሱት እና ማኅበረ ቅዱሳን ላይ እጃቸውን የሚቀስሩቱ ለሃይማኖቱ ክብር ባለው  በትግራይ ሕዝብ ታንቅረው የተተፉ ለመሆናቸው እማኝ የሆንኩባቸው አጋጣሚዎች ሆነው አልፈዋል።ዛሬ የማስታወሻ ደብተሬን እንዳነሳ ያደረገኝ ሰሞኑን የተያዘው አዲሱ የቤተ ክህነት አማሳኞች እና የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት ቦታ የለየ አስመስሎ የሚያቀርብ ፅሁፍ በማየቴ ነው።በዛሬው እለት በወጣው ፅሁፍ ላይ ”የአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ገዳምን ስም ማኅበረ ቅዱሳን ለማንሳት ይፀየፋል” የሚል ሙሉ በሙሉ በውሸት የተለወሱ አረፍተ ነገሮች ይነበባሉ።የሚገርመው ነገር ገዳሙ ተረስቶ እና  የሚያስበው አጥቶ በብዙ ድካም እና መንገላታት ከቦታው ደርሶ ለገዳሙ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ቀርፆ ለገዳሙ ያስረከበ  ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ፀሐፌው አለማወቃቸው ምን ያህል በመረጃ ዘመን ከመረጃ የራቁ መሆናቸውን አመላክቶኛል።አልያም ሃይማኖትን ለማመስ ከአማሾች ጋር የተባበሩም  መሰሉኝ። ለሁሉም ማኅበረ ቅዱሳን በምን አይነት ፈተና ወደ አባ ሰላማ ገዳም  ተጉዞ ፕሮጀክት እንደቀረፀ እና እንደተገበረ ይህንን  ማያይዣበመክፈት  ፊልሙን ይመልከቱ እና ይታዘቡ።

ጉዳያችን
ጥቅምት 11/2007 ዓም (ኦክቶበር 21/2014)

ምንጭ:

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35582

ቦሼን ምን ነካው? ባሰበት እኮ!!!

አሜጋ ነኝ ከኖርዌይ (chinchaw94@gmail.com)

ቦሼን ምን ነካው

ሰው ሲመራና ሲመራ (ለስልጣን ለማለት ፈልጌ ነው) መቼም ለየቅል ናቸው። ስልጣን ይዞ ህዝብን ማስተዳደር ሲጀምር 99 በመቶ ሊባል ይችላል የሰው ልጅ ባህሪው ይቀየራል በይበልጥ እንደእኛ  ሃገር ታዳጊ በሆኑት ላይ። ግለሰቡ ስልጣኑን ሲጨብጠው ህዝብ መሆኑን ይረሳና ሁሌም ባለስልጣን እንደሆነ የሚቀር ይመስለዋል፤ ነገር ግን ወደ ህዝብነቱ የተመለሰ ቀን ወየውለት ነው የሚባለው ሌላ ምን ይባላል። ኧረ እስቲ ወደ ቦሼዬ ልምጣ!

አቶ ቦሼ በዚህ ወር ለፓርላማው በዲሲ ዲያስፖራዎች የተደረገውን የኢምባሲ ወረራ ሲናገሩ ሰምቼ በሳቅ የሞትኩ መሰላችሁ ነገረ ስራቸው እርር ድብን ነው ያደረገኝ (ለሳቸው ሞራል ስል ነው እርር አልኩ ያልኩት፤ካፈለጉ ርሳቸው ከነጦሳቸው እርር…)። ምን ቢሉ ጥሩ ነው በውጭ ሃገራት መኖር ሳይሳካላቸው ሲቀር የሻዕቢያ ቅጥረኛ ሆነው በመላላክ እያሸበሩ፣ እንዲሁም የሻዕቢያን ፍርፋሪ እየለቀሙ የሚኖሩ ቅጥረኞች፣ ገዳዮች እያሉ በዲሲ የደረሰባቸውን ሽንፈት ሲያስተባብሉ፣ ሌላም ሌላም…። ታዲያ ይሄኔ ነው አቶ ቦሼን ኧረ ትልቅ ሰው ነዎት ሼም፣ ሼም ያልኳቸው። መች ይሰማሉ!!! አንዴ ፈርዶባቸው የራዕዩ መሪ መንፈስ ተጠናውቷቸው። እኔን ምን እንደገረመኝ ታውቃላችሁ? የሻዕቢያን ፍርፋሪ እየለቀሙ ያሏት ነገር!!! ለመሆኑ ሻዕቢያ እንኳን ለኢትዮጵያኑ ፍርፋሪ ልትሰጥ ለራሷ የሚላስ የሚቀመስ የሌላት መሆኗን የአደባባይ ሚስጥር ነው። እናም የምትበላው የላት የምትከናነበው አማራት ሆነብኝ ሻዕቢያ ለአቶ ቦሼ። ገዳዩስ ማን ሆነና፣ አየነው እኮ ወዲን በደደቢት የለመደውን በአሜሪካ ሲደግመው። በአለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪ ብሎ የተመደበው ህውሃት ወያኔ እንጂ ምስኪኑ ዲያስፖራ አይደለም። ጥሩ ሰው ነበሩ ይባላል ዱሮ ድሃ ሆነው፣ምን ነካዎት?  ልቦናና የሚያስብ ጭንቅላት ቢኖርዎት ኖሮ እነኝህ ያልተሳካላቸው አሸባሪ የተባሉት ኢትዮጵያኖች የሚልኩት ብርና ሃገሪቷ የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ባላጋንን ከዋናው ኤክስፖርት ምርታችን ቡና ባይበልጥ ነው!!! ይህን እንኳን ማገናዘብ ነበረብዎት።

ሌላው ቅጥፈታቸው የኢትዮጵያ መንግስትና ሌላው ኢትዮጵያዊ (የወያኔ ደጋፊ ማለታቸው ነው) ከገዳዮቹ ማለትም ከአሸባሪዎቹ ጋር ግብግብ የፈጠሩበት አንድም ጊዜ የለም … አቦ ትንሽ ይደብርዎታ! ውሸትም ሲበዛ እኮ!!!! ከቪዲዮ በላይ መረጃ ምን አለ? አቶ ቦሼ ከበታች የለጠፍኳቸውን ቪዲዮዎች ጋበዝኩዎት ሌላ ምን ይባላል፣ ያዘንኩት ግን ያች የተቀደሰች ሃገር በርስዎ ቀጣፊ ስትመራ በጣም ያሳዝናልም ያሳፍራልም!!! የምመክርዎ በዱሮ አለቃዎት ላይ ምን እንደደረሰ ያስቡና ወደ አዕምሮዎት ይመለሱ። ካስታወሱ ባለራዕዩ መሪዎት እጅ እንቆርጣለን፣ ባንዲራ ጨርቅ ነው፣ ሌላም ሌላም ያሉበት ልሳን ተዘግቶ ምንም ሳይሉን ላሽ ብለዋል።

ኧረ ደግሞ ክቡር የሆነው ባንዲራችንን መሬት አውርደው ሲሉ ትንሽ ትንሽ አይሰቀጥጥዎትም? ደፋር ነዎት፣ ምን ያድርጉ የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛዋል አይደል፤ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሆነ የወደቀ ዛፍ ሆኗል ማንም እንደልቡ እየመጣ ይፈነጭብናል። ፊቱን ያዞረ ቀን ግን …። ባልደረባዎ ባንዲራ ጨርቅ ነው እያሉ እንዳላፌዙብን እርስዎ ደግሞ  ዞር ብለው ክቡሩ ባንዲራ ይሉናል… ፌዝ አይሆንም? ህዝብስ ላይ ማላገጥ አይሆንም? ለማንኛውም ጊዜ ይፈታዋል።

አቶ ቦሼ (ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ቦሼ) በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዲን ሆነው ሲሰሩ በጣም መልካምና ትሁት እንደነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ። ታዲያ አሁን ምን ነክቷቸው  ነው ውሸት፣ ቅጥፈት ያበዙት። ከአህያ የዋለች ጊደር ሆኖባቸው ይሆን? እንደዛ ከሆነ አሁንም ጊዜ አለዎትና እራስዎትን ከወያኔ ቅጥፈትና ንቀት ትምህርት ቤት አውጥተው ወደ ህዝቡ ይመለሱ። አለበለዚያ ግን ስልጣንዎትን ተመክተው እንደፈለጉ የሚያፋሽጉ ከሆነ ህዝብ የሆኑ እለት ምን እንደሚገጥምዎ ግልፅ ነው። እናም አቶ ቦሼ ወደ ህሊናዎ ይመለሱ!!!

መንግስት ከአሸባሪ ግብግብ አልገጠመም ላሉት ይኸው

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን ላሉቸው (ባጭሩ ወያኔ ቢሏቸው) ግብግብ የለም ላሉት ይኸው፣ Shame on you