ኖርዌይ ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በግዳጅ ወደ ሀገራቸው ለመመሰስ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረገችውን ስምምነት የሚቃወም ታላቅ ሰልፍ በታላላቅ የኖርዌይ ከተሞች ተካሄደ!!

Posted by አሜጋ (ከኖርዌይ)

ኢትዮጵያውያን በስደት ከሚኖሩባቸው የተለያዩ የአውሮፓና ስካንዴኔቪያን ሀገሮች አንዷ የሆነችው ኖርዌይ ስትሆን በኖርዌይ ሃገር ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ስደተኞች ይገኛሉ። እነዚህ ስደተኞች ከሌላው ሀገር ለየት የሚያደርግ ጠንካራ የፓለቲካ አቋም ያላቸው መሆኑም ይታወቃል። ስደተኞቹ በተለያየ ጊዜያት የገዢውን ፓርቲ ብልሹ አስተዳደር የሚያጋልጡ የፓለቲካ ስራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል።
ሆኖም ግን የኖርዌ መንግስት እ.ኤ.አ በ2012 ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ጋር በኖርዌይ የሚኖሩ ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስገድዶ ወደ ሃገር ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። ሆኖም ግን ይህ ስምምነት በተለያዩ ምክንያቶች ተግባር ላይ ሳይውል ቀርቷል። ኖርዌይ በድጋሚ አሁን በያዝነው አመት በፌብርዋሪ ወር እንደገና ስደተኞችን አስገድዶ ወደ ሀገር የመመለሱ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ቴዎድሮስ አደሃኖም ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በኖርዌይ የሚገኙ ታላላቅ የዜና አውታሮች ሰሞኑን ሲዘግቡ ሰንብተዋል።

0328351be332f7a63ab778c6aecd8c3f_M

ይህንኑ ስምምነት አስመልክቶ በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር ስምምነቱ ትክክል እንዳልሆነ ተቃውሞውን ለመግለፅ በማርች 15፣ 2016 ሰልፍ አዘጋጅቶ ነበር። ይህ የተቃውሞ ሰልፍ በሶስት ታላላቅ የኖርዌይ ከተሞች፦ በኦስሎ፤ በበርገን እና እስታቫንገር ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በታላቅ ተቃውሞ ተካሂዷል። ስደተኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተለይ በቅርቡ በሀገራችን በአደባባይ እየተገደሉ ያሉ ወገኖቻችንን የያዙ ምስሎችንና የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውና ከደቡብ ሱዳን ታፍነው በኢትዮጵያ እስር ቤት እየማቀቁ ያሉንት የአቶ ኦኬሎ አኳይ ፎቶግራፍ እንዲሁም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ፎቶግራፎች በመያዝ ስለነሱም አያይዞ ለኖርዌይ ፓርላማ ተወካይ ጥያቄ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ እየታወቀ ሰዎች በየሰከንዱ እየተገደሉ ባለበት ወቅት ሀገሪቱ በብዙ አቅጣጫ የህዝብ አመፅ ባለበትና ገዢው ፓርቲም ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ሰዎችን እየገደለና እያሰረ ባለበት ጊዜ ስደተኞችን አስገድዶ ለመመሰል ስምምነት ማድረጉ ለምን እንዳስፈለገ፤ እንዲሁም የኖርዌይ መንግስት ለኖርዌጅያን ዜጎች በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች መዘዋወር አደገኛ መሆኑን መግለጫ እየሰጠ ባለበት ሁኔታ የፓለቲካ ስደተኞችን አሳልፎ መስጠት ሰብአዊነት የጎደለውና የስደተኛ መብት ህግን የሚጥስ መሆኑን ኢትዮጵያውያኑ በሰልፉ ላይ ተናግረዋል።

በሰልፉ ላይ ከተለያዩ ድርጅቶች የተወከሉ ተወካዮች ንግግር ያደረጉ ሲሆን በኖርዌ የስደተኛ መብት ተከራካሪ የሆኑ የኖርዌጅያን ድርጅቶችም በሰልፉ ላይ ተገኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደሚያውቁና ስምምነቱንም እንደማይደግፉ አቋማቸውን ገልፀዋል። በመጨረሻም የስደተኛ ማህበሩ ሊቀመንበር የስደተኛውን የአቋም መግለጫ በማንበብ ሰልፉ በተያዘለት ሰአት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ኢትጵያ ለዘላለም ትኑር
የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዌይ!!

ምንጭ:-

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/52294

አቶ ዘመነ ምህረት ተፈቱ – መኢአድ ጠቅላላ ጉባዬ ሊያደርግ ነው – ሳተናው

Posted by አሜጋ (ከኖርዌይ)

ጥር 10 ቀን ነው ከሚኖሩበት አካባቢ ታፍነው የተወሰዱት። አቶ ዘመነ ምህረት የመኢአድ ም/ፕሬዘዳንት፣ አቶ መለሰ መንገሻ የመኢአድ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊና አቶ ጌትነት ደረሰ የመኢአድ አባል። ሽብርተኛ” ናችሁ በሚል ክስ ታስረው ወደ ማእከላዊ ይወርዳሉ። በማእከላዊ ከፍተኛ ቶርቸር ይፈጸምባቸዋል። እጅግ የሚዘገንን ስቃይ። በአንድ የጅስ መዝገብ ዉስጥ ተካተው ለብዙ ቀናት ፍርድ ቤት ተጉላሉ።

አቶ ዘመነ ከቀረበባቸው ክስ መካከል “በጥምቀት በዓል በጎንደር ቦምብ ልታፈነዳ ነበር፣ ከግንቦት ሰባት ጋር ትሰራለህ ፣ የሻእቢያ ተላላኪ ነህ” የሚል ክስ ነበር። ለዚህ ክስ አቶ ዘመነ ” እኔ ጎንደር ተወልጄ በጎንደር ባህል እና እምነት ተኮትኩቼ ያደግሁ ክርስቲያን ነኝ የቀረበብኝ ክስ በጥምቀት በዓል ላይ ቦንብ ሊያፈነዳ የሚል ክስ አለበት ይህ ፈፅሞ ሀሠት ነው እኔ ይህንን እንዳደርግ እምነቴም እድገቴም አይፈቅድም ይህንን እንኳን እኔ ክርስቲያኑ ግራኝ መሃመድ እና ደርቡሾችም አላደረጉም። እኔ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) አመራር እና የፕሮፌሰር ዓስራት ወልደየስ አላማ እንዲፈፀም የምደክም ሠላማዊ ታጋይ ነኝ። ፕሮፌሰር ዓስራት ደግሞ የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ ጉዳዩን በግልፅ የተቃወሙት ነው። እንዴት እኔ የሻዕቢያ ተላላኪ ልሆን እችላለሁ?” የሚል ምላ ነበር ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጡት።

አንድ ወንጀለኛ ክስ ሲመሰረትበት ፈረንጆች preliminary hearing የሚሉት ከሁለት ሶስት ሳምንታት በላይና ከ3፣ 4 የፍርድ ቤት ቀጠሮ በላይ የማይፈጅ የፍርድ ሂደት ይደረጋል። የፍርድ ቤት ጊዜና የሕዝብ ገንዘብ እንዳይባክን፣ ዳኛው አስቀድሞ ለክስ የሚበቃ በቂ መረጃ መኖሩን የሚያይበት ነው። አቃቢ ሕግ የከሰሰበትን መረጃ ያቀርብና ዳኛው ተከሳሹ ይከላከል ወይንም የአቃቤ ሕግ ክስ  መሰረት የሌለው ነውና ክሱ ክርክር ሳይደረግበት ዉድቅ ይደረግ የሚለውን ይወስናል።

እነ ዘመነ ቢያንስ አሥራ ስምንት ጊዜ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል። ጥር 10፣ ሚያዚያ 8፣ ግንቦት 6 ፣ ግንቦት 27 ፣ ሰኔ 11፣ ሰኔ 16፣ ሐምሌ 1፣ ሐምሌ 2፣  ሐምሌ 21፣ ነሐሴ 4፣ ነሐሴ 13 ቀናት 2007 ዓ.ም፣ ጥቅምት 12፣ ህዳር 3፣ ህዳር 23፣ ጥር 4፣ የካቲት 25፣ መጋቢት 5፣ መጋቢት 8  2008 ዓ.ም። በመጨረሻ መጋቢት 8 ቀን 2008 ዓ.ም ፣ አቶ ዘመነ ምህረት የሽብርተኝነት ክሳቸው ወደ ወንጀል ክስ ተቀይሮ በዋስ ሊለቀቅይ ችለዋል። አቶ ጌትነት ደርሶ በሽብርተኝነት ክስ ተከላከሉ በመባላቸው አልተፈቱም። አቶ መለሰ መንገሻ ፣ በፍርድ ሂደቱ መሃከል ተከሰው የነበሩት “የአርበኞች ግንባር አባል ነህ” በሚል ስለነበረና የአርበኞች ግንባርም በፓርላማ ሽብርተኛ ተብሎ ያልተወሰ በመሆኑ፣ የሽብርተኝነት ክሱ አይመለከተኝም ብለው በማመልከታቸው፣ የርሳቸው ጉዳይ በሌላ መዝገብ እንዲያይ ተደርጓል።

አቶ ዘመነ ከእሥር ከወጡ በኋላ ለመኢአድ አባላት ፣ ደጋፊዎችና ለነጻነት ናፋቂው ህዝብ በሶሻል ሜዲያ መልእክት እንደሚከተለው አስተላልፈዋል፡

“ውድ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ ያላችሁ ከአንድ አመት ከሁለት ወር የስቃይ እስራት በኋላ ለጊዜው ከጠባቡ እስር ቤት ወደ ሰፉው እስርቤት ወጥቻለሁ እስራት ለኛ ለመኢአድ ልጆች አዲስ አይደለም በዚህ በ23 ዓመት የተሠጠን ስጦታ ነው አሁን ታስረናል ወደፊትም ዘረኛው ህውሃት ባንዳው ብአዴን እስካ ድረስ አማራ መሆን ወንጀል ነው ስለዚህ ይህ አገዛዝ እስካልተወገደ ድረስ እስራት ፣ ምት የማይቀር ነው መፍትሔው ሁላችንም ይህንን ስርአት ለማስወገድ በጋራ እንነሳ “

አቶ ዘመነ እሥር ቤት በነበሩባቸው ወቅቶች ደርጅታቸው መኢአድ ትልቅ ፈተና ገጥሞት እንደነበረ የሚታወቅ ነው። በተለይም የደርጅቱ ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪ አመራር ለድርጅቱ መዳከምና ለአባላት መከፋፈል እንደ ዋና ምክንያት ይጠቀሳል። የተከፋፈለዉን የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎች በማሰባሰብ ዙሪያ ትልቅ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ የሚባሉትና በብዙ የመኢአድ አባላት ዘንድ ከበሬታ ያላቸው አቶ ዘመነ በመኢአድ ዉስጥ ስለሚኖራቸው ሚና ብዙ የገለጹት ነገር ባይኖርም፣ ከመታሰራቸውም በፊት በአቶ አበባው አመራር ላይ እርሳቸውም ቅሬታ እንደነበራቸው ይናገሩ ነበር።

መኢአድ በቅርቡ ያደርጋል ተብሎ በሚጠበቀው ጠቅላላ ጉባኤ፣ አቶ አበባው መሐሪ ከሃላፊነታቸው ይነሳሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የአቶ አበባው መነሳት በመኢአዶች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት እና መኢአድ ጠንካራ ሆኖ እንዲወጣ ለማድረግ ሁኔታዎችን የበለጠ ያመቻቻል ተብሎም ይጠበቃል።

ምንጭ:-

http://www.satenaw.com/amharic/archives/14732

በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ የታቀደው ድቡቁ የህወሓት ሴራ ሲጋለጥ | ምስጢራዊ መረጃ

Posted by አሜጋ (ከኖርዌይ)

ከዚህ በታች የምታነቡት በትግረኛ ተጽፎ የህወሓት ባለስልጣናት የተወያዩበትና የተስማሙበት ድብቅ መረጃ ነው። ይህ ረቂቅ ዶኩመንት በወያኔም ባለስልጣናት ተቀባይነት አግኝቶና ጸድቆ በተግባር በአስቸኳይ በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ህዝብ ላይ በተግባር ላይ እንዲውል ስምምነት ተደርሶበታል።
ይህ በትግረኛ የተዘጋጀውና ወደ አማርኛ የተተረጎመው ሰንድ የተዘጋጀውና በህወሃት ባለስልጣናት እንዲተገበር ያቀረበው በብዕር ስሙ ዘጽኣት አናንያ በሚል ስም የሚታወቅ እውነትኛ ስሙ ግን ጎይቶኦም የማነ ገብረኣናንያ የተባለ ቀንደኛ የህወሃት ስውር ፊታውራሪ ነው።
ከትግረኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመውን ከዚህ ቀጥሎ ያንብቡ። በትግረኛ የተጻፈው በመጨረሻዎቹ ገጾች ላይ ማንበብ ይቻላል።

ባለፉት 15 ኣመታት በትንሽ ግለሰቦች ሲነሳ የቆየ ባሳለፍናቸው ትንሽ ኣመታት ደግሞ የተቃውሞ ቅርፅ እየያዘ እየመጣ ያለው በምዕራባዊ ዞን ወረዳ ጠለምትና ግላዊ ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች በኣሜሪካ በሚገኙት የሰሜን ጎንደር ወልቃይት ጠገዴ እድርና በጎንደር ህብረት በሚባሉ የስምሪት ኣሰላለፍ እየተረዱ ይመለከተናል በሚሉት የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ኣካባቢ እጆጃቸው ለኣንዳችም የልማት ስራ እንኳ ሳያነሱ ለነዚያ የግል ቅሬታ ያለባቸው ሰዎች በማሰባብሰብ የገንዘብ፣ የሞራልና ሓሳብ ምክር ሙሉ ድጋፍ በመስጠት ለኣራቱም የትግራይ ወረዳዎች ነዋሪዎች የኣማራ ማንነት ጥያቄ እንዳላቸውና በማንነታቸው ወደ ሚመስላቸው የኣማራ ማንነት ሊመለሱ እንደሚፈልጉ በማስመሰል ህዝብ ያልጠየቀው ጥያቄ በመያዝ ከህግ ውጭ የማንነት ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ፌደረሽን ምክር ቤት፣ የኣማራ ክልል ርዕሰ ኣስተዳደርና ሌሎች የፌደራል ኣካላቶች እንደደረሳቸው በተለያየ መልክ ተሰራጭቷል።

ይህ ጉዳይ ሕጋዊ ለማስመሰልና ለማሰራጨት ሰንደቅ ጋዜጣ በ28 ቀን 2008 ዓ/ም ዕትም ኣድምቆ ለማቅረብ ሞክሯል። ከዚህ በተጨማሪ በትምክህተኞች ሃይል የሚመሩ ሚዲያዎች እየተሰራጨና እየተስፋፋ መጥቷል ፤ እየመጣም ነው። ከዚህ በመሻገር ደግሞ በውጭ ከሚገኙ ሚሊዮን ዶላሮች ለዚህ ኣላማ ለማዋጣት ዝግጁነታቸው በማጠናቀቅ ለጦርነት እስከ የማነሳሳት ስራ ለመስራትና ከጎጃምና ኣብዛኞቹ የጎንደር ወረዳዎች የገንዘብ እርዳታ የሚደረግላቸው በቀን ሰራተኛነት ስም ወደ ምዕራባዊው የትግራይ ዞን (ወልቃይት፣ጠገዴ፣ ቃብቲያና ሁመራ) በብዛት በማስገባት ኗሪ ለማድረግ በተዘጋጁብት ግዜ እና ከኣማራ ክልል ኗሪ ለዚህ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ከጎናቸው በቆሙበት ስኣትና በትንሽ የብኣዴን ኣመራር ካድሬዎች ኣይዟችሁ እያሉ ባሉበት ስኣት ትግሬዎች እንደትግሬነታችን ተነሳስተናል ወይ የሚል ጥያቄ እንድታነሳ ያድርጋል። የዚህ ምልክት በዚህ ሳምንት በፌስቡክ የተለቀቀው የ13 ደቂቃ የቅስቀሳ ቪድዮ በቋራ ይካሔድ ወይንስ በኣርማጭሆ ብዙ ሰው በተገኘበት ዳስ ተጥሎ የመብልና የመጠጥ ግብዣ ተደርጎ ቅስቀሳ ሲደረግ ከላይ ያለውም ሆነ ታችኛው የብአዴን ኣመራር ኣያውቅም ማለት የዋህነት ነው።

ስለሆነ በትግራይስ እንደ ህወሓት ምንና ምን ስራዎች እየተሰሩ ነው የሚል የብዙ ትግሬዎች ጥያቄ እንኳን ቢሆንም በሚስጥር እየተሰራ ከሆነ ጥሩ ሆኖ ሳለ ህወሓት በመሬት ጉዳይ ተዝናንታ ስትቆይና በድረስ ድረስ ባለቀ ስኣት ብትሯሯጥ ግብ ሳይመቱ የመቅረት የነበሩዋት ክፍተቶች ኣሁንም እንዳይከሰት እንድትጠራጠር ያደርግሃል። ይህ በኢትዮጵያ የመንግስት ሽግግር ግዜ የኣማራና ትግራይ ክልል ሲከለሉ የነበረው የህወሓት ቅንነት ግን ደግሞ የብአዴን ተንኮል ታይቷል። ለምሳሌ፦ ግልፅ በሆኑ ኣከባቢዎች በግልፅ የሚወሰድ ሲሆን በእነዛ የሁለቱም ብሔረሰቦች የሚገኙበት ኣካባቢ ማለትም የትግርኛ ተናጋሪዎችና የኣገዉኛ ተናጋሪዎችም ተደበላልቀው የሚኖሩበት ከሰቆጣ እስከ ኣበርገሌ ፊናርዋ የትግርኛ ተናጋሪ ነህ ወይስ የኣገውኛ እየተባሉ በሚጠየቁበት ግዜ በብአዴን የተሸረበ ተንኮል ለሁለቱም ቋንቋ እኩል የሚችላቸውን ህዝብ ትግርኛ ትችላለህ ሆይ ተብሎ ሲጠየቅ ኣልችልም የሚል ጭንቅላቱ ነቅንቆ ምልክት ሲያሳይ በተቃራኒው ደግሞ ኣገዉኛ ትችላለህ ሆይ ተብሎ ሲጠየቅ ኣዎ ብሎ መልስ እንዲሰጥ ውስጥ ለውስጥ ተሰርቶበት በኣብዛኛዎቹ ድል ሲቀናቸው በተወሰኑ የፊናርዋ ኣካባቢና በግማሽ የኣበርገሌ ኣካባቢ ተደናቅፈው በዚህ ምክንያት ፊናርዋ ከፊል የኣበርገሌ ወደ ትግራይ ሲሆኑ እነዛ ብዙዎቹ ቀበሌዎች ግን ወደ ኣማራ እንዲከለል ተደርጓል፤ ይህ የክልሎች መነሻ ክለላ ስለነበረ ብዙ ጥያቄዎችን ኣላስነሳም። ከክልላችን ውጭ ባሉ ስንመለከት ደግሞ ከ1998 እስከ 2008 ዓ/ም የይገባኛል ጥያቄዎች የሶማሊ ክልል ከኦሮሚያ ክልል ፤ የደቡብ ክልል ከኦሮሚያ ክልል በሁለቱም በኩል ጥያቄ የተነሳበት ኣከባቢዎች በፌደረሽን ምክር ቤት ወደ ሪፈረንደም እንዲቀርብ በማድረግ ልክ ይሁን ኣይሁን እልባት ተደርጎበታል። ለምሳሌ፦ በሶማሊና ኦሮሚያ ክልል የተነሳው የይገብኛል ጥያቄ ከመኢሶና ኣዋሽ ወንዝ ጥግ እስከ የኬንያ ኣዋሳኝ የሚዘልቅ ብዙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ያቀፈ ነበር። በዚህ ሁኔታ ሁለቱም ክልሎች ኮሚቴ ኣቋቁመው የሪፈረንደም ቀን የሚያደርስ የስብከትና ብዙ ሚሊዮን ብር በጣም ብዙ ሺ ኩንታል ስንዴ እና ሩዝ እንዲሁም ዘይት ለህዝቡ በዋነኝነት ለጎሳ መሪዎችና የኣገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ተሰሚነት ላላቸው ወገኖች ሲሰጡ ከቆዩ ብሗላ የቋንቋቸው ተናጋሪዎች እንደስጦታቸው መጠን፣እንደ ስብከታቸው፣ ተንኮላቸውና ቅልጥፍናቸው መጠን ወረዳዎችና ቀበሌዎች ኣግኝተዋል። በኦጋዴን ሰራዊት መከላከል ምክንያት ደካማ ውስጣዊ ኣሰራር የነበረውን የሶማሊ ክልል የተሻለ የኮሚቴዎች ኣወቃቀር፣ ብር፣ ስንዴና ሩዝ የነበረው የኦሮሚያ ክልል በጣም በበለጠ ሁኔታ ድል ሊቀናው ችሏል። በኣሁኑ ስኣት ኣብዛኞቹ የሶማሊ የነበሩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በማጉረምረም ላይ ናቸው። ተታለን ወደ ኦሮሚያ ሔደን ኣሁን ልጆቻችን ቋንቋቸውን ትተው በኦሮምኛ በግድ እየተማሩ ነው፤ ያለ ቋንቋችንና ኣስተዳደራችን እየተዳደርን ነው ይላሉ። ይሁን እንጂ የማይመለስ ንስሓ መሆኑ ግን በሚገባ ተረድተዋል።
ይህ ከላይ የተገለፀው በእኛ ላይ እንዳይደገም እኛ ትግሬዎች ምን ብናደርግ ነው የሚሻለው?

የወልቃይት ጠገዴና ኣካባቢዎቹ የታወቁ የናይዝጊ ልጆች መሆናቸው ያ መሰረቱ የማይጠፋው የናይዝጊ ቤተ መንግስትና የትግርኛ ታናጋሪዎች መሆናቸውን የሚያጠያይቅ ስላልሆነ የፅሑፍ ሓተታ ኣያሰፈልገንም። ታዲያ ለምን? ቢሉ ከፊላችን እያወቅን ከፊላችን ደግሞ በየዋህነት እንዳንዘናጋ ወይ ደግሞ ብአዴን ያን ውስጣዊ የክልላዊ ስልጣን ተቀባይነቱ ለማናር ብሎ ብአዴን ህዝብ እየጠዬቀ ነው በሚል በግልፅ ጥያቄው ለፌደረሽን ምክር ቤት ሊያቀርብ ስለሚችል ሳንታለል ተዘጋጅተን መቆየት ስልያስፈልገን ነው። ይህ የተንኮል ምልክት በታየባቸው የምዕራባዊ ዞን ኣካባቢዎች ብቻ ሰርተን የምንተኛ ሳይሆን በራያ ኣንዳንድ ኣካባቢዎችም በልዩ ሁኔታ ደግሞ ራያ ኣላማጣ፣ ኦፍላ፣ በኮረም ከተማና ኣላማጣ ከተማ ጭምርም ሊሰራበት ይገባል። ለዚህ ደግሞ በግልፅና በውስጣዊ ኣሰራር ሊተገበሩ የሚገቡ ኣንገብጋቢ መርሃ ግብሮች ኣሉ።
እነዚህም፦

ሀ. በግልፅ ሊሰራባቸው የተገቡ መርሃ ግብሮች

የህወሓት ፓርቲ ገዢዎችና በትግራይ ክልል ብቻ የተመሰረቱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከመወነጃጀል ስራ ነፃ ሆነው በትግራይ የበላይነት ኣላማ ኣምነው የዚህ ክልልና ሃገር እድገት ለማረጋገጥ የኣቋምና የመተማመን የምናይበት ግዜ እየናፈቀን ነው። ይህ ኣሁን ያለንበት ግዜ ደግሞ ይሔን ጉዳይ ኣጥብቆ የሚፈልግበት ሁኔታ መሆኑ ማስተዋል ይጠይቃል። በኦሮሚያ ያሉ ተቃዋሚዎችና ገዢው ኦህዴድን ብናይ በሉኣላዊነትና የህዝብ የድህንነት መብትና ተጠቃሚነት የተዋሃዱና የተናበቡ ሆነው ይታያሉ።

በወረዳዎች ያለው የመልካም ኣስተዳደር እጦትና በሕብረተሰቡ መሰላቸትና ማጉረምረም ስለሚፈጥር ለእነዚህ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች የሚበቅሉበት በማዳበሪያ የተዘጋጀ ለም መሬት በራሳችን እየፈጠርንላቸው ስላለን በኣፋጣኝ የሚታረምበትና ስርኣትና መልክ የሚይዙበት ሁኔታ መፈጠር ኣለበት። ወደ ምዕራባዊው የትግራይ ዞን (ወልቃይትና ጠገዴ) የሚላኩት የተሾሙ የዞንና የወረዳ ኣመራሮች፣ የፍትህ ኣካላት በደጋማው የትግራይ ኣካባቢዎች ደካማ የስራ ኣፈፃፀም ያላቸውና ጥፋትም ያላቸው በቅጣት መልክ ወደ ኣካባቢው እንዲላኩ መደረጉ፤ መምህራን፣ የጤና ባላሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ደግሞ ለስራቸው መጀምሪያ ልምድ እንዲያገኙበት እንዲሆን ተደርጎ የተፈረደበት ኣካባቢ ነው። ይህ ደግሞ በኣካባቢው ልማትና መልካም ኣስተዳደር ትልቅ ኣሉታዊ ተፅእኖ ኣለው።

የመፍትሔ ሓሳብ፦

ያ ኣካባቢ በልማት ተጠቃሚ የሚሆንበትን በተጠቃሚነቱ በጎረቤቱ ከሚገኙት የኣማራ ክልል ወረዳዎች የተሻለ የልማት ተጠቃሚ ሆኖ በሚያይበት ግዜ ትግሬነቱ ኣጠናክሮ የሚቀጥልበትና ለሚመጡ የትግሬነቱ ጠላቶች በጣም ኣጠንክሮ የሚዋጋበት ሁኔታ ስለሚፈጥር በዚህ ጉዳይ በጣም ተጠናክሮ ቢሰራበት ዘላቂ መፍትሔ ያስገኛል። በተጨማሪ ከምዕራባዊው የትግራይ ዞን ውጭ ብንመለከት እንኳን በደርቅ የተጠቁ የኣማራ ክልል ወረዳዎች ዋግሀምራና ራያ ቆቦን በቂ የሰውና እንሰሳ ምግብና የመጠጥ ዉሃ ሲቀርብላቸው በኣንፃሩ ደግሞ በእነዚህ ኣከባቢ የሚገኙ የኣማራ ክልል ኣዋሳኝ የሆኑ የትግራይ ወረዳዎች እንደ ጣንቋ ኣበርገሌ፤ ሰሓርቲ ሳምረና ራያ ለሰዉና እንሰሳ የሚያስፈልግ ምግብና የመጠጥ ውሃ ከጅምር በዘለለ የሚታይ ስራ ኣለ የሚያስብል ኣይደለም። ራያ ቆቦ ከከርሰ ምድር በሚገኝ ውሃ በመስኖ ሲለማ በኣንፃሩ ደግሞ ቀድሞ የተጀመረው የራያ መስኖ ስራ በትግራይ ስላልተሰራበት የራያ ትግራይ ህዝብ ለልማት ተጠቃሚነት ሲል ወደ ኣማራ ክልል ከሔድን እንደራያ ቆቦ እንለማለን የሚል መንፈስ ፈጥሮ ችግር እስከሚፈጠር ድረስ እንዲያድግ ሰለማያስፈልግ በፍጥነት መፍትሔ ቢደርግለት ኣሁንም ጠቀሜታን ያስገኛል።

ሀ. በውስጣዊ ኣሰራር ሊተገበሩ የሚገባቸው መርሃ ግብሮች

1. ለእነዛ ከህግ ውጭ ኮሚቴ ኣቋቁመው በኣካባቢውና በውጭ (በኣሜሪክ ኣውሮፓና ሌሎች ኣግሮች) እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ኮሚቴና ኣባላቶቹ ጉዟቸው የሚደናቀፍበትና በተጓዙበት ሁሉ እንቅፋት እንዲያጋጥማቸውና ተስፋ እንዲቆርጡ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል። ይሔም በዛ በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ባሉ ትግሬዎችና የትግራይን ጣዕም በሚገባ የሚያውቁ ኣካላት በሚስጥር ሊሰራና ሊከናወን ይችላል።

እነዚያ ኣባላቶቹ ጉዟቸው የሚያቋርጡበትና ከሕብረተሰቡ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጫና እንዲያድርባቸው መስራት ያስፈልጋል። በዚህ የማይመለሱ ከሆነ ደግሞ ከሕብረተሰባቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚለዩበት ስራዎች መስራት የግድ ይለናል። ለዚህ ሃሳብ የሚያንቀሳቅሱ ኣባላት፣ ኮሚቴውና ተባባሪዎቻቸው ከማህበራዊ ኣገልግሎት እንዲገለሉ መስራት፤ሆቴል ፣ መኪና ወዘተርፈ እንዲጠቀሙ በሚቀርቡበት ግዜ ለባለንብረቶቹና ኣግልግሎት ሰጪዎቹ የማንቂያ ሰራ በመስራት እነርሱ የሚፈልጉትን ኣገልግሎት እንዳያገኙ በማድረግ ባለንብረቶቹ ግዴታዎቻቸው እንዲወጡ መስራት ያስፈልጋል።

2. ይህ የትግራይ የቆላ ኣካባቢ ህዝብ (ምዕራባዊው ዞን)በደጋ ከሚኖረው የትግራይ ህዝብ ጋር ስነ-ልቦናዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲደለደል ማድረግ። የወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ ወረዳዎች ካለፉት መንግስታት ጀምሮ እስከ ኣሁን ድረስ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቱና ማዕከሉ የጎንደር ከተማ ብቻ እንዲሆን ነው የተፈረደበት። የንግድ ሸቀጣ ሸቀጦች ከፋብሪካ ውጤቶች እስከ ኣትክልቶችና ፍራፍሬዎች የሚቀርብለት ከጎንደር ብቻ ነው። ለተጨማሪ የግል ትምህርት ልጆቹ የሚጓዙት ወደ ጎንደር ነው፤የሱዳን ሸቀጣ ሸቀጦች የሚገኝበት በመተማ በኩል ነው፤ በትግራይ ምዕራባዊው ዞን (በወልቃይት ጠገዴና ቃብቲያ ሁመራ) እንደምንም ተጠጋግቶ ተጣቦ ኣርሶ ብር ያጠራቀመ ሰው ሲኖር ህንፃና የንግድ ቤቶች የሚሰራበትና የሚከትምበት ጎንደር ወዘተርፈ…ይህ በጣም ሓይለኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ጫና ፈጥሮ ስለሚገኝ ይሔን ችግር ለመቀልበስ ደግሞ ደረሰኝ የሌላቸው ሸቀጣ ሸቀጦች ከጎንደር እንዳይመጡ የክልከላ ጫና ሰለባ እንዲሆን በማድረግ በተቃራኒው ከደጋማው የትግራይ ኣካባቢ ጋር ግንኙነት ለማጠናከር ደግሞ በሽሬና መቀሌ የሚገኙ ታላላቅ ነጋዴዎች በልዩ ሁኔት በማናገር በኣከፋፋዮች ደረጃ ከሁሉም ዓይነት የንግድ ዉጤቶችና ሸቀጣሸቀጦች ከጎንደር ከሚመጣው ንብረት ሁሉ በጣም በቀነሰ የዋጋ መጠን ቢያንስ ግን ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ሙሉ ብሙሉ የሚሸፈንበት መንገድ በኣጭር ግዜ ውስጥ መፈጠር ኣለበት። ከሽሬ ጀምሮ በሉግዲ በኩል የተዘረጋው ጥርጊያ (ሱዳንና ትግራይ የሚያገናኘው የጥርጊያ መስመር) በጣም ተጠናክሮ በፍጥነት እንዲሰራበትና ይህ የጥርጊያ መስመር እንዲጠናከር በጣም ጠንክሮ መስራትና ማገዝ፤ በዚህ ጉዳይ ከሱዳን ጋር በጥልቅትና በፍጥነት መወያየት ያስፈልጋል።

የትግራይ ኪነ-ጥበብ በተለይ የትግርኛ ዘፈኖች ብናያቸው በሁሉም ዘፈኖቹ ሲጠሩ የምንሰማቸው የኣካባቢ ስሞች ትግራይ ማለት ከሽሬ የሚመለስ እንደሆነ የሚሰብኩ ናቸው። ይህን ችግር ከመሰረቱ በማረም ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሁመራ ያካተተ እንዲሆን የትግራይ ጥበበኞች እንዲያስቡበት ማድረግ፤ ምክንያቱም በኣማርኛ ቋንቋ የሚዘፈኑ የጎንደር ኣካባቢ ስም የሚያነሱ ዘፈኖች ሁሉ ብንመለከት ኣሁንም ያልተዋቸው በሽታ የእነዚህ ኣካባቢ (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሰሜን፣ኣርማጭሆ፣ጠለምትና ሁመራ) ስም ሳይጠሩ ኣያልፉም። ስለሆነም የጥበብ ድርሻ በሰው ልጅ ስነ-ልቦና ከፍተኛ ተፅእኖ ስላለው የትግራይ ጥበበኞች ልንሰራበት ይገባል። የቆላው የትግራይ ተወላጅ (ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ፣ ቃብቲያና ጠለምት) ከጎንደር ታሪክ በላይ በኣክሱምና ይሓ ታሪክ ኩራት እንዲሰማዉና የእኔነት ስሜት እንዲያድርበት ማድረግ የግድ ያስፈልጋል። ከኣጤ ቴድሮስ ታሪክ በላይ የኢትዮጵያን ዳርድንበርን ለማስከበር ላይ እና ታች እያለ ሳለ የሞተውን የኣጤ ዮሃንስ ኣራተኛ ጀግንነት ኣውቆ እንዲኮራበትና እንዲመካበት ቢደረግ የትምክህተኞቹ የኣማራዎቹ ተግባር ማለትም ከድሮ ጀምሮ በተዋረድ የመጣውን ክፋታቸውና ዉሸታቸው እንዲሁም የትግራዋይን ስም የማጥፋትና በወሬ በማስተጋባት ብልግና እንደሰሩ በማስተማር በተቃራኒው ደግሞ የትግራይና ትግራዎትን የበላይነትንና ብሔርተኝነትን ከፍ በማድረግ በውስጣዊ ስብከት እንዲያስተጋባ በማድረግ ጫና መፍጠር።

3. የሐይማኖት ኣባቶች ግዴታዎች፦
በኣካባቢው ኣብዛኛው የኦርቶዶክስ ሐይማኖት እምነት ተከታይና የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆኑ በኣብያተ-ክርስቲያናት ላይ የሚደረጉት ስብከቶችና ኣገልግሎቶች ከኣማርኛ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንዲሆኑ በማድረግ በትግርኛ እንዲገለገሉ ማድረግ። በኣከባቢው ወደ ሚገኙ ኣብያተ-ክርስቲያናት የሚመደቡ ገበዝ፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ከኣካባቢ ሰዎች እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ ኣገልጋዮች ከሁሉም የደጋው የትግራይ ኣካበቢ የሚመደቡበት ሁኔታ በማመቻቸት የመስበኪያ ቋንቋ ትግርኛ እንዲቆጣጠረው ማድረግ። ይህም ማለት ያ ኣሁን ያለው የኣካባቢው የኣብያተ-ክርስቲያናት ኣገልግሎት የኣማርኛ ቋንቋ የበላይነት የሚያራምዱ የጎንደሬዎችና የጎጃሞች ቋንቋ ለትግርኛ ቋንቋ የሚቆጣጠረው ስለሆነ ነው።

4. የኣካባቢው ተወላጅ የሆኑ ተሰሚነት ያላቸው የኣገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት መሪዎችና ሃብታሞች ትግሬነታቸው እንዲኮሩበትና ለእነዛ በመሓል ስሜት ያሉ ሰዎች ሰብከው የሚያመጡበት ሁኔታዎች ለመፍጠር መነጋገርና መግባባት በመፍጠር እንዲሰሩበት ማድረግና በልዩ እንክብካቤ መያዝ ያስፈልጋል።

5. የኣካባቢው ኗሪ ተወላጆች በመንግስት ስራዎችና በግል ስራዎች በሁሉም የትግራይ ደጋማው ኣካባቢ ከሚኖሩብት የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ማድረግና ከትግራይ ነጋዴዎች ጋር ጥብቅ ሁኔታዎችና ግንኙነት እንዲኖር መፍጠር። በተቃራኒው ደግሞ ወደ ትግራይ ምዕራባዊው ዞን የደጋማው የትግራይ ህዝብ በብዛት በማምጣት ቋሚ ኑሮ የሚኖርበትና የሚመራበት ሁኔታዎች በመፍጠር ይህ መርሃ ግብር በፍጥነት እውን እንዲሆን ማድረግ ኣስፈላጊ ነው።

6. ኣዳዲስ የሰፈራ ማዕከሎችን በማቋቋም በሸራሮና ሁመራ የጥርጊያ መስመር ፈቃደኛ የወልቃይትና የጠገዴ ተወላጆች በዛ ኣድርገን ከሌላ ኣካባቢዎች ኣደባልቆ በሰፈራ ማዕከሎች ማስፈር። በኣማራ ክልል ድንበር የሚገኙ ኣዋሳኝ የወልቃይትና የጠገዴ ቀበሌዎች ላይ ከትግራይ በሚመጡ ሰፋሪዎች በቋሚነት እንዲሰፍሩና በእርሻና ንግድ በጣም ፈጣንና ጠንካራ እንዲሆኑ በማድረግ የተለያዩ የብድር ኣገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም ግብር እንዳይከፍሉ በማድረግ በቋሚነት የሚኖሩበት ሁኔታ ማመቻቸት።

7. በባላባት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆችና ለስራ ከደጋው የትግራይ ኣካባቢበሔዱትና በሚሔዱት የትግራይ ተወላጆች መካከል በትዳር በሰፊው እንዲገናኙ በማድረግ የትግራይ ልጆች ኣንድነት እንዲጠነክር መስራት ያስፈልጋል። በመጨረሻ እነዚህ የመሳሰሉትን የሚነሱ ጥያቄዎች የሚከታተል ውስጣዊና ሚስጥራዊ ኮሚቴ በማቋቋም መፍትሔዎችን ያፈላልጋል፤ በትምክህተኛ የኣማራ ሓይል በኩል የሚደረጉ ዉስጣዊና ዉጫዊ እንቅስቃሴዎች በትኩረት መከታተል ያስፈልጋል።

wolqit1

wolqite 3

wolqite2

ምንጭ:-

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/52155

ኩዌት ያላችሁ ኢትዮጵያዊ እና ኤርትራዊያን ጥንቃቄ | ቀን እስኪያልፍ…

Posted by አሜጋ (ከኖርዌይ)

በግሩም ተ/ሀይማኖት

ስለኩዌት መረጃውን ያገኘሁት ግሩፕ ውስጥ ስገባ ነው። ኤልዳና ፖስታዋለች አነበብኩት። ይጠቅማል እሰራለሁ ትንሽ ለውጥ አገኛለሁ ብሎ ለሚያስብ ጥንቃቄ ይሻል። ወደው ከኮንትራት ቤት አልጠፉ..
ኩዌት ውስጥ የምትገኙው ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ኤርትራውያን ራሳችሁን ጠብቁ:: የኩዌት መንግሥት የተለያዩ ሀገር ዜጋዎችን መንገድ ላይ በማስቆም ፍተሻ እያረገ ነው። ፓስፖርታቸው ያልታደሰ በህገ-ወጥ መንገድ የገቡ እንዲሁም ከዚይ በፊት በተለያየ ነገር የተጠረጠሩ… እንዲሁም ህጋዊ ያልሆኑትን በማሰር ወደ ሀገራቸው እንመልሳለን ብለው ፍተሻውን አጡፈውታል::

qw

qw2
የመኖሪያ ወረቀት ያላችሁም ስትንቀሳቀሱም ፓስፖርታችሁን መያዝ አትርሱ። በተለይ ግን ተገፍታችሁ እና መከራ ሆኖባችሁ ከኮንትራት ቤት ወጥታችሁ ፓስፖርት እጃችሁ ላይ የሌለ ፓስፖርት ኖሯችሁ መኖሪያ ፍቃድ የሌላችሁ አብዝታችሁ ጥንቃቄ አድርጉ። 


ኢትዮጵያውያን ሰንት እንደተያዘ ባይታወቅም ፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ስደተኞች ናቸው። ክፉውን ያርቅልን።
አሜን!!!!!

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/52165

የህወሓት ቡድን የወልቃይትን ህዝብ ጉሮሮ ፈጥርቆ እስትንፋሱን ሊያቋርጠው ተግቶ እየሰራ ነው

Posted by አሜጋ (ከኖርዌይ)

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
የህወሓት ቡድን የወልቃይትን ህዝብ ጉሮሮ ፈጥርቆ እስትንፋሱን ሊያቋርጠው ተግቶ እየሰራ ነው፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከትግራይ አጓጉዞ በአራት የሰፈራ ጣቢያዎች ላይ ሊያሰፍር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

“ህወሓት መሬታችንን እንጂ እኛን አይፈልገንም…” የሚሉት የወልቃይት ነዋሪዎች ዛሬ ዛሬ የሚፈፀምባቸው መከራ ከመቸውም ጊዜ በላይ በርትቷል፡፡ ግፍና በደሉ ምድሪቷን አጥለቅልቋል፡፡ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰዎች በህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች እየታፈኑ ደብዛቸው እየጠፋ ነው፡፡ በስውር እየተገደሉ ነው፡፡ የህወሓቶች ሰፋፊ እስር ቤቶች በወልቃይት ነዋሪዎች ተጨናንቀዋል፡፡

የወልቃይት ህዝብ ይህ ሁሉ መከራ፣ ግፍና ሰቆቃ እየተፈፀመበት የሚገኘው “ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ” በማለቱ ብቻ ነው፡፡ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ተደራድሮ ለመፍታት ያቋቋመው ኮሚቴ አባላት በህወሓት እየተሳደዱ ነው፡፡ አቶ በለጠ ታደሰ እና አቶ ማሩ ሽፋ የተባሉት የኮሚቴው አባላት የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍነው “የህዝቡን ሃሳብ አስቀይራችሁ ትግሬ ነኝ እንዲል ካላደረጋችሁ በስተቀር በምድር ላይ አትኖሩም…” የሚል ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በኋላ ተለቀዋል፡፡ ከየካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሁለቱ ኮሚቴዎች የት እንደተወሰዱ ሳይታወቅ ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡

የወልቃይትን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለማፈን የህወሓት ቡድን ከግድያው፣ አፈና እና እስሩ ባሻገር የተለያዩ ሸፍጦችን እየፈፀመ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከትግራይ አጓጉዞ በወልቃይት ምድር ላይ በአራት ሰፈራ ጣቢያዎች ለማስፈር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በሁመራ እና በሌሎች የወልቃይት ከተሞች የሚገኙትን ሆቴሎች፣ ህንፃዎችና የንግድ ቦታዎች የስርዓቱ ታማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች እንዲከራዩዋቸው እየተደረገ ነው፡፡

በመሆኑም ወልቃይቶች ተዕግስታቸው እንደተሟጠጠና ጠብመንጃቸውን በመወልወል ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡ “በግንቦትና ሰኔ አንዱ ይለያል” በማለት ቆርጠው መነሳታቸው ተሰምቷል፡፡

 

Breaking: የኤፍኤም 97.1 ራድዮ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሥርዓቱን ከድተው ለንደን ሄደው በዛው ቀሩ

Posted by አሜጋ (ከኖርዌይ)

Breaking News zehabesha

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኤፍ ኤም ራድዮ የሆነው fm97.1 ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አንድነት ለንደን ለስራ ተልከው በዛው መቅረታቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋለጡ::

በገዢው መንግስት ቁጥጥር ሥር የሆነው በዚሁ ኤፍ ኤም ራድዮ ላይ የሚተላለፉ ለከት የሌላቸው የመንግስት ፕሮፓጋንዳዎች እና የሚታፈኑ የሕዝብ ድምጾች እንዳበሳጫቸው የሚገለጽላቸው አቶ አንድነት ስርዓቱን በመክዳት ለንደን ቀርተዋል::

የኢትዮጵያ መንግስትን በመቃወም ሥር ዓቱን የሚከዱ አባላት ቁጥር እየጨመረ ይገኛል:: በቅርቡ በርካታ ፌደራል ፖሊሶች ከነትጥቃቸው ሥር ዓቱን ከድተው ወደ ኤርትራ መግባታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

የፌዴሬሸን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት መጋዘን ተዘረፈ

Posted by አሜጋ (ከኖርዌይ)

የኢሕአዴግ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ግዙፉ ቅጽር ግቢ ውስጥ የሚገኘው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት መጋዘን ላይ ዘረፋ መካሄዱ ተሰማ፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ዕቃዎች ማከማቻ መጋዘን ዝርፊያ፣ የካቲት 19 ወይም 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ሳይከናወን እንዳልቀረ ተገልጿል፡፡ መጋዘኑ ተሰብሮም በርካታ ኮምፒዩተሮች መዘረፋቸው ታውቋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ገብሩ ገብረ ሥላሴ መጋዘኑ ሥራ በሌለባቸው የእረፍት ቀናት ተሰብሮ አሮጌ ኮምፒዩተሮች መዘረፋቸውን ለሪፖርተር አረጋግጠው፣ ዕቃዎች መጥፋታቸው የታወቀው የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ሠራተኞች ወደ ሥራ በሚገቡት ወቅት መሆኑ ጠቁመዋል፡፡

‹‹ጉዳዩ በፖሊስ የተያዘና በመጣራት ላይ ያለ በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አይቻልም፤›› ብለዋል፡፡ የኢሕአዴግና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም ፊት ለፊት የሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚገኙበት ግዙፍ ቅጽር ግቢ፣ በፌዴራል ፖሊስ ጥብቅ ጥበቃ የሚደረግበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ነገር ግን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ይህ ጥበቃ እየተደረገለት እንዴት ሊዘረፍ እንደቻለ ግርምት እንደፈጠረባቸው ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡ ጥብቅ ጥበቃ ከሚደረግበት ግቢ አሮጌ ኮምፒዩተሮችን መዝረፍ በራሱ አነጋገሪ ከመሆኑም በላይ፣ ምናልባት ከኮምፒዩተሮቹ ሐርድ ዲስክ ውስጥ መረጃዎችን ለማሸሽ ሊሆን ይችላል የሚል መላ ምት እየተሰነዘረ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩ በመጣራት ላይ ስለሆነ መረጃ ለመስጠት  ጊዜው አይደለም ብሏል፡፡

ምንጭ:-

http://www.ethiopianreporter.com/

Breaking: ከአምቦና ወሊሶ ወደ አዲስ አበባ የሚወስድ የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ቆሟል

Posted by አሜጋ (ከኖርዌይ)

የምትመለከቱት ፎቶ ዛሬ በቡራዩ አካባቢ ሲሆን ታክሲዎች ሥራ በማቆማቸው በመንግስት አስገዳጅነት አይሱዚዎች ያገኙትን ሰው እንዲህ ጭነው እንዲሄዱ እየተገደዱ ነው:: ሰልፉን ተመልከቱት:: የታክሲ ሾፌሮች አምርረዋል::

በመንግስት አስገዳጅነት አይሱዚዎች ያገኙትን ሰው እንዲህ ጭነው እንዲሄዱ እየተገደዱ ነው::

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት የአዲስ አበባ ታክሲዎች አድማ መምታታቸውን ተከትሎ ዛሬ ጠዋትም አልፎ አልፎ የመንግስት ካድሬዎች ከሚነዷቸው ታክሲዎች በስተቀር የታክሲዎች አድማ እንደቀጠለ ነው::

ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የአዲስ አበባ ታክሲዎች የሥራ ማቆም አድማ ወደ ክልል የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ተዘዋውሯል:: ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ; ከወሊሶ ወደ አዲስ አበባ እንዲሁም ከጉደር ወደ አዲስ አበባ የሚያመላለስ የሕዝብ ተሽከርካሪ እንደሌለም ተሰምቷል::

ይህ ሕዝባዊ ቁጣ በተለያዩ ክልሎች እንደሚቀጥልም ይጠበቃል:: መንግስት ታክሲዎች በአስቸኳይ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ዛሬም ተቃውሞው ቀጥሏል።

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ የትራንስፖርት ችግር ተከሰቷል

Posted by አሜጋ (ከኖርዌይ)

በአዲስ አበባ የሚገኙ የታክሲ ሹፌሮች የወያኔ አገዛዝ ያወጣውን የትራንስፖርት እና መንጃ ፍቃድ ሕግ በመቃወም የጠሩት የስራ ማቆም አድማ በዛሬው እለት የአዲስ አበባን መንገዶች ከትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ውጪ በማድረጋቸው ተገልጋዩ በትራትስፖርት ችግር ሲገጥመው ተስተውሏል::

የአዲስ አበባን የታክሲ ሹፌሮች ከስራ ውጪ ለማድረግ እና ስራ ፈት ዜጎችን ለመፍጠር ታስቦ በወያኔ የወጣው አዲስ ሕግ ማንኛውም ሹፌር 21 ጊዜ ጥፋት ካለበት መንጃ ፈቃዱ ተነጥቆ ከሹፌርነት ለመጨረሻ ጊዜ የሚያግድ ሲሆን የታክሲ ሹፌሮችን ሆን ብሎ በማጥቃት ከስራ ውጪ በማድረግ የደህንነት አካላት የሆኑ አዳዲስ እየሰለጠኑ የሚገኙ የሕወሓት አባላትን የታክሲ ባለቤቶች ላይ ጫና በመፍጠር በሹፌርነት ለማሰማራት የታቀደ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ::

የወያኔው አገዛዝ በተለያዩ በዝባዥ እና ሕዝብን በሚበድሉ ሕጎች ኢትዮጵያውያንን እያሰቃየ ሲሆን ይህም ከፍተኛ የሆነ ብሶት አደባባይ ላይ መሰማቱ ሲቀጥል የስራ ማቆም አድማውም የዚሁ ብሶት አካል መሆኑ ታውቋል::በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ተገልጋዮች በተለያዩ መንገዶች ትራንስፖርት ለማግኘት ቢሞክሩም እንዳልቻሉ ታይተዋል::የወያኔ አገዛዝ ለሶስት ወር አራዘምኩት ይሕጉን ተግባራዊነት የሚል መግለጫ ቢሰጥም ተቀባይነት አጥቶ የስራ ማቆም አድማው ተደርጓል::ሕዝቡ ብሶቱን በተለያየ መንገድ በመግለጽ ስርኣቱ እንዲወገድ ትግሉን ቀጥሏል::